ህዳር 19/2016 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን፣ዞን አቀፍ የህዝብ የውይይት መድረክ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
“በአዲስ ምእራፍ፣በአዲስ ተስፋ፣አዲስ ክልል” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን ከማህበረሰቡ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የህዝብ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የንቅናቄ መድረኩ በክልሉና በዞኑ ያሉ ጸጋዎችን በመረዳት ወደ ልማት መቀየር የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ህዝብና መንግስትን ለማገናኘት ታልሞ የተዘጋጀ ህዝባዊ የውይይት መድረክ መሆኑንም እንደሆነ ተገልጿል።
በመድረኩም በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማዕረግ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ፣የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ ጁሀር፣የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ጨምሮ የክልልና የዞኑ የስራ ኃላፊዎች ከየወረዳና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።