የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

======================

ሙስና በአንድ ሀገር ላይ ዜጎች ለድህነት ፡ ለልመናና ለጉስቁልና እንዲዳረጉ ሰፊ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ሁሉም አምሮ ሊታገለው እንደሚገባ ተገለፀ።
በጉራጌ ዞን እዣ ወአዳ አለም አቀፍ የፀረ -ሙስና ቀን በዓል “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በጋራ እንታገለው ” በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።
የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ በዚሁ እለት እንደገለፁት ያለው ውስን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም በተለይም የሙስና አስከፊነት በመገንዘብ ማህበረሰቡ ብሎም ቤተሰብን በማስተማር በተቀናጀ ትግል ሙስናን መከላከል ያስፈልጋል ።
የመንግስት ሀብትና ንብረት በሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዳይባክን ሲቪል ሰርቫንቱ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በመታገልና በሀገሪቱ ልማትና እድገት ላይ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ም/አስተዳዳሪው ጨምረው ገልፀዋል።
ሙስና በአንድ ሀገር ላይ ዜጎች ለድህነት ፡ ለልመናና ለጉስቁልና እንዲዳረጉ ሰፊ እድል የሚፈጥር ነው ያሉት አቶ ተጠምቀ በመሆኑም በያለንበት አካባቢና የስራ ዘርፍ የሙስና መገለጫ የሆኑ አሰራሮች እንደ ግዢ ስርዓት ፡ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችና ሌሎችም ላይ ሁሉም በመረባረብ ሙስናን ቢያንስ ባለበት ማስቆም ይገባልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ፀረ-ሙስና ጥምረት ኦፊሰር አቶ ይብሮ ሁሴን በበኩላቸው እንደ ወረዳው ሙስናን አስቀድሞ ለመከላከል የግንዛቤና ሌሎችም ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በተለይም የስነ-ምግባር ባለሙያ ያለባቸው ተቋማት ላይ እንደ ወረዳ በመቀናጀት በተቋማት ብልሹ አሰራሮች እንዳይፈጠሩ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በወረዳው ሙስናን ለመከላከል በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በ2015 ዓም ከተቋማት ኦዲት 1070141 ብር ተመላሽ መደረጉን የጠቆሙት ኦፊሰሩ ለወጣቶች የስራ ኦድል ፈጠራ ከተሰራጨው ብድር 1.6 ሚሊየን ተመላሽ መሆኑን ክትትል ተደርጓል ብለዋል ።
በቀጣይም በየተቋማት በጥቆማ የሚመጡ ሙስናዎችና ብልሹ አሰራሮች የሚታረሙበት መንገድ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅኖጅት ለመስራት አስፈላጊውን ጥረት ይደረጋልም ብለዋል።
አስተያየት ሰጪዎች በሰጡት አስተያት ሙስና የተሰጠውን ስራ በአግባቡ ካለማከናወን እንደሚጀምር አንስተው በቀጣይም እንደወረዳው የሚገጥሙ ብልሹ አሰራሮችን በመታጋል የእርጥት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ሁሉም በጋ መታገል ይገባል ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።