የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

===================

በወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ በባለፉት 6 ቀናት 222 ሰዎች ነፃ የአይን ሞራ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ህክምናው የተሰጠው በአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሲሆን ህክምናው የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ከኦርቢስ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር እንደሆነም ተጠቁሟል ።
የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ እንደገለፁት የአይን ሽፋሽት ወደ ውስጥ መቀልበስ ችግር ወይንም የአይን ሞራ ያለባቸው ሰዎች ህክምና ካገኙ የማዳን እድል ያላቸው ሲሆን ካልታከሙ ግን የአይነ ስዉርነት ችግር የሚያስከትል በመሆኑ የህብረተሰቡ ችግር ሆኖ እንዳይቀጥል የበለጠ አጽእኖት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ።
እንደ ወረዳውና ከተማ አስተዳደር የዚህ ችግር ያለባቸው ሰዎች እንዲታከሙ ሰፊ የሆነ የቅስቀሳ ስራ በመስራት በአቅራቢያቸው በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች አስቀድሞ የመለየት ሰራ መሰራቱን የገለፁት ሀላፊው በተለይም በዚህ ዙር የአይን ሞራ ያለባቸው ከተለዩ በኋላም ከህዳር 3 -8/2016 ዓም በአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 222 የሚሆኑ ሰዎች ህክምና አግኝተዋልም ብለዋል ።
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በመንግስት ያልተሸፈኑ አቅሞችንና ክፍተቶችን ለመሙላት እየሰራ ነው ያሉት አቶ መሀመድ ይህም አርያነት ያለው ስራ በመሆኑ በወረዳው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አንዳንድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አካላት በሰጡት አስተያየትም ለረጅም ጊዜ ለማየት የአይን ብርሃናቸውን እጅግ አስቸጋሪ ወቅቶች ማሳለፋቸውን አስታውሰው አሁን ግን በነፃ በተደረገላቸው ህክምና ድነው ለማየት መብቃታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል ።
ይህም ህክምና ላስተባበሩ አካላት ታካሚዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።