የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

========

ነገ ሀገር የምትገነባው በተማረው ትውልድ መሆኑን ጠንቅቃ የተረዳችው አርቆ አሳቢ ብርቱዋ “ዘነበች ታዳሰ ” ዛሬም ልማት ላይ ናት ።
ለብቻዋ አንድ ትምህርት ቤት ከነ ሙሉ ቁሳቁሱ ገንብታ ለመንግስት ያስረከበች ጀግኒት ዘነበች ታደሰ ትምህርት ቤቱ ወደ ሰባተኛ ክፍል ድረስ እንዲያድግ ተጨማሪ የክፍል ግንባታዎችና ቁሳቁሶች ከማሟላት በተጨማሪ እንደምትመለከቱት የተማሪዎች ምቹ የሆነ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ በዶዘር እያሰራች ትገኛለች ።
የጉራጌ ባህላዊ ምግብ ዝግጅት አምባሳደሯ ዘነበች ታደሰ /ዮኸሚያ ክትፎ ባለቤት / በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ጉየና የስዋ ቀበሌ ዮጊያር አካባቢ ተወልዳ ያደገችው ሲሆን ህፅናት ትምህርት ፍለጋ ሩቅ መንገድ እንዳይጓዙ በአካባቢያቸው በቅርብ እርቀት እንዲማሩ የነበራት የልጅነት ህልሟ በእውኑ ያሳካች ድንቅ ሴት ናት ።
የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ;ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንደ ወረዳው በርካታ ባለሀብቶችና ተወላጆች አካባቢያቸው ብሎም ወረዳውን በሁሉም መልኩ ለማልማት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ይገልፃሉ ።
በተለይም በአሁን ወቅት ” ጋበር” የተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር በማቋቋም በትምህርት ፡ በጤናና በሌሎችም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ አስደማሚ ስራዎች በመስራት ላይ መሆናቸውን አቶ ተጠምቀ ጨምረው ይገልፃሉ ።
ወ/ሮ ዘነበች ታደሰም ሙሉ ትምህርት ቤት ከመገንባታቸው ባለፈ ትምህርት ቤቱ ገንብተው ለመንግስት ብቻ አስረክበው የሄዱ ሳይሆን በየጊዜው ትምህርት ቤቱ በመጎብኘት ለተማሪዎች የዓመት የትምህርት ቁሳቁስ ማለት እስክርብቶና ደብተር ገዝተው ያስረክባሉ ።
ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎችን በመሰብሰብ የእሷ ተሞክሮ እያካፈለች ጎበዝ እና ነገ ተምረው ለሀገር እንዲጠቅሙ በመምከር እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በየጊዜው የሚያስፈልጉ ነገሮች በቅርበት ሆኗ የምትከታተል ትልቆ ጀግና ሴት በመሆኗ የወረዳው መንግስት እሷንና መሰል የልማት ጀግኖች ከልብ እንደሚያመሰግን አቶ ተጠምቀ መልዕክት አስተላልፈዋል።