የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

==============================

ህዳር 26/2016
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የስንዴ መውቂያ ቴክኖሎጅ በማሻሻል ተግባር ላይ አውሏል!! በኮሌጃችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰልጣኝ መ/ር  አንዋር ቶፊቅ አማካኝነት የተሰራውና ናሙና ፍተሻ ተደርጎበት ማሻሻያ ሀሳቦች ከተጠቃሚዎች ተሰጥቶበት የነበረው የገብስ መውቂያ ቴክኖሎጂ ዳግም በማሻሻል ስራ ላይ አውሏል።ቀደም ሲል ለገብስ መውቂያ አገልግሎት ብቻ የነበረው ቴክኖሎጂ ለስንዴና ለጤፍ ጭምር መውቂያ እንዲሆን ተደርጎ የተለያዩ አሰልጣኞችና ጽናት ኢንተርፕራይዝ ተሳትፈውበት ማሻሻያ ተደርጎበታል። ይህ ቴክኖሎጂ በአሁን ወቅት በተሳካ ሁኔታ በስንዴና ገብስ ማሳ ላይ ተሞክሮ ውጤታማነቱ በማረጋገጥ ሙሉ በሙሉ ተግባር ላይ የዋለ ሲሆን በቀጣይ ከፍተኛ መጠን ያለው ምርት በአጭር ሰዓት ወቅቶ የመጨረስ አቅም እንዲኖረው መጠኑ ከፍ ተደርጎ እንዲሰራላቸው አንድ አንድ ከፍተኛ ሄክታር መጠን በገብስ/ስንዴ ምርት የሚሸፍኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በጠየቁን መሰረት ይህንን ትኩረት አድርገን አገና ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የዘርፉ ኢንተርፕራይዞች ጋር በቅንጅት የምንሰራ መሆኑን ከአሰልጣኞቻችን ጋር የጋራ አቅጣጫና ተግባቦት ላይ ተደርሷል።በመጨረሻም ለዚህ ቴክኖሎጂ ማሻሻል መሳካትና ወደ ተግባር እንዲገባ ጥረት ያደረጋችሁ አሰልጣኞች በሙሉ በእዣ ወረዳ ማህበረሰብ ስም ከልብ እናመሰግናለን።