
==========================================
ህዳር 29/2016>>>>>አስደሳች ዜና!!
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ እጅግ ዘመናዊና የተሟላ መረጃ ከየትኛውም ቦታ ማግኘት የሚያስችል ድህረ-ገፅ አበለፀገ!!
ኮሌጃችን በዓይነቱና በይዘቱ እጅግ ዘመናዊ: የተሟላ መረጃ ማግኘት የሚያስችል: በሞይባልም ሆነ በኮምፒውተር ለመጠቀም እጅግ ቀላልና አመቺ: ለሰልጣኞቻችንና ለአሰልጣኞቻችን የተሟላና ጥራት ያለው ስልጠና ለማሳለጥ የሚረዱ የስልጠና ሰነዶች የያዘ:የኢንደስትሪዎች መረጃ:አዲስ ለሚመዘገቡ ሰልጣኞች ስለ እያንዳንዱ ስልጠና ዘርፍ ሰፊ ማብራሪያና ያሉ የስራ-ገበያ አማራጮች በቂ ገለጻ ያለው እና በአጠቃላይ የኮሌጃችን ተግባራት በማቀላጠፍ ለማህበረሰባችን ብሎም ለአለምአቀፍ ማህበረሰብ በቀላሉ ስራዎቻችን ተደራሽ በማድረግ አለም አቀፍ አጋርነትን ማጠናከር የሚያስችል www.agenacollege.edu.et የተሰኘ እጅግ ዘመናዊ ድህረ-ገጽ በአሰልጣኝ መ/ር ስንታየሁ ፈለቀ አማካኝነት አበለፀገ።
ኮሌጃችን ይህንን ዘመናዊ ድህረ-ገጽ በቀጣይ ታህሳስ ወር ለባለድርሻ አካላት ዝርዝር ገለጻ በማድረግ በይፋ የሚያስመርቅ ሲሆን ከወዲሁ www.agenacollege.edu.et የሚለውን ጽሁፍ በማንኛውም የዌብሳይት መፅሃፊያ አፕ( google chrome, internet explorer, etc ) ላይ በመፃፍ መጎብኘት የሚቻል መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!!
ለማንኛውም አስተያየት:
#1. admin@agenacollege.edu.et
#2. info@agenacollege.edu.et






©2023. የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከአገና ኮንስትራክሽን እና ኢደስትሪያል ኮሌጅ ጋር በመተባበር. All Rights Reserved.