ቀን 05/03/2016 ዓ.ም
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋናንስ ለእዣ ወረዳ ባህል ቱሪዝም የጉራጌ ባህል ልብስ በግልጽ በጫረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቹ እና የዘመኑ ግብር በመክፈል ፍቃድ ያደሳችሁ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / ቲን / ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በእቃ አቅራቢነት የመተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደወሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ 10,000(አስር ሺህ ብር ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ( ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸዉ እቃዎች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶክሜንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100( አንድ መቶብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ቀን 27/03/2016 ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዳቸው ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ክ/ን/አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸ ቀን ጀምሮ በ 7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማሲያዝ ውል መፈጸም አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨራታዉ ማሸነፋቸውን ከተገለጸበት ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ውል ማስከበሪያ አስርቶ ውል ካልፈጸሙ መስሪያ ቤቱን የጨረታ ማስከበሪያ የመውረስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቶች የጨረታውን ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናን እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜ ኣና እሁድ እንዲሁም የባአል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል፡፡
- ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋዘ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው 15 በቀን ታሽጎ በዚህው እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈገታ፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቶች የተጫረቱባቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበበት ጀምሮ ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡
–ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 011 3 29 03 17 /011 3 29 03 18/ 011 3 29 02 60/ 011 3 29 00 06
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
አገና