የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ህዳር 16/2016 ዓ.ም
በአጭር ፣በመካከለኛና በረጅም ርቀቶች የተሻለ ሰአት ያስመዘገቡ ተተኪ ወጣት አትሌቶች በመመልመል የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑም የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።
በዛሬዉ እለት በኩፐር ቴስት ዉድድር ነባር አትሌቶች አቅማቸዉን የሚፈትሹበትና በየዉድድሩ የተሻለ ሰአት ያስመዘገቡ አዳዲስ አትሌቶች ወደ ክለቡ ለመቀላቀል ዉድድር እየተደረገ ይኛል።
በአጭር ፣ በመካከለኛና በረጅም ርቀቶች አወዳድረዉ ወጣት አትሌቶችን የመለየትና ወደ ክለቡ የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ነዉ።
የጉራጌ ዞን አስተዳድር ጽህፈት ቤት ሀላፊና የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ እንዳሉት የአትሌቲክስ ክለቡ በዞኑ በርካታ አቅም ያላቸዉና ተተኪ አትሌቶች የምናፈራበት ክለብ ነዉ።
በሩጫዉ ዘርፍ በዞኑ ከፍተኛ አቅም ያላቸዉ ወጣቶች መኖራቸዉም አመላክተዉ ለአብነት ያህል ዞኑን ብሎም ሀገሪቱን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድረዉ ዉጤት እያመጡ የሚያስጠሩ አትሌቶች በርካቶች መሆናቸዉም አስረድተዋል።
ክለቡ በማቋቋም የዞኑ አስተዳድር ከምስረታዉ ጀምሮ የሚያስፈልገዉ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተናግረዉ በዘንድሮ አመትም ለክለቡ አትሌቶች የሚያስፈልጋቸዉ ነገሮች ለማሟላት የሚቻለዉን ጥረት እንደሚያደርግም አስረድተዋል።
ክለቡ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረዉ በማድረግ የበለጠ ዉጤታማና የሚፈለገዉን ስኬት እንዲጎናጸፍ የባለ ድርሻ አካላት ፣ ባለሀብቶችና የሌሎችም የማህበረሰብ ድጋፍና እገዛ ወሳኝ እንደሆነም አስታዉቀዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሄኖክ አብድልሰመድ እንዳሉት የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ በአጭር ፣በመካከለኛና በረጅም ርቀቶች በሀገር አቀፈና በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ አትሌቶችን በማፍራት ይታወቃል።
የዘቢደር አትሌቲክስ ክለብ ለማጠናከር አትሌቶች በየአመቱ የምዘና ዉድድር የሚያደርጉና በተጨማሪም ለክለቡ አቅም የሚሆኑ አትሌቶች ከፕሮጀክት በመመልመል በየዉድድሩ የተሻለ አቅምና ጥሩ ሰአት ያስመዘገቡ አትሌቶች ወደ ክለቡ እንዲቀላቀሉ ይደረጋል ብለዋል።
አትሌቶች በሀገሪቱ በተለያዩ ክለቦች እንዲገቡና እንዲሳተፉ እገዛና ድጋፍ እንደሚደረግላቸዉም አመላክተዉ በክለቡ የታቀፉ አትሌቶች ዉጤታማ እንዲሆኑ እያሳዩት ያለዉን ተነሳሽነትና ጥረት የበለጠ አጠነክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉም አብራርተዋል።
ዞኑ ለአትሌቲክስ ስፖርት ምቹና አስተማማኝ ከመሆኑም በተጨማሪ አካባቢን የማስተዋወቅ ስራም እየተሰራ እንደሆነም አስታዉቀዉ የኩፐር ቴስት ዉድድሩ የትሌቶችን አቅም የሚፈተሽበትና በቀጣይ ተተኪ አትሌት ለማፍራት እንደሚያግዛቸዉም ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርትመምሪያ ምክትል ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደም ሽኩር እንዳሉት የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ በ2004 ዓመተ ምህረት የተመሰረተ ሲሆን በየአመቱ የኩፐር ቴስት ዉድድር ይደረጋል ብለዉ ይህ ዉድድር ክለቡን የበለጠ ለማጠናከር ያግዘዋል።
በኩፐር ቴስት ዉድድር በዋናነት ነባር አትሌቶች አቅማቸዉን የሚፈተሽበት ፣በዞኑ በፕሮጀክት ታቅፈዉ ሲሰሩ የነበሩ አትሌቶች እድል የሚፈጠርበት መድረክ እንደሆነም አብራርተዋል።
ክለቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአትሌቲክሱ ዘርፍ እያደረገዉ ያለዉን አስተዋጽኦ የጎላ ከመሆኑም በተጨማሪ በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ አትሌቶችን የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች እያፈራ ይገኛል ብለዋል።
አሁን ላይ ክለቡ ጥሩ አቅም ላይ እንዳለም ያመላከቱት አቶ አደም ከክለቡ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በግልና በፌዴሬሽኑ አማካኝነት ዉድድር እያደረጉ ያሉ አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በግልና በፌዴሬሽኑ አማካኝነት ዉድድር እያደረጉ ያሉ አትሌቶች መኖራቸዉም አመላክተዋል።
በምልመላዉ በአጭርና በመካከለኛ የተሳተፉ ወጣት አትሌት ሰላም መለሰና አትሌት ቃሲም ተማም በሰጡት አስተያየት በፕሮጀክት ታቅፈዉ ልምምድ ሲያደርጉ የቆዩና ዛሬ ወደ ዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ለመቀላቀል ምልመላዉን እየተሳተፉ እንደሆነም አመላክተዋል።
በመጀመሪያ የማጣሪያዉ ዉድድር ከአምናዉ የተሻለ ሰአት ማስመዝገብ እንደቻሉና ፍጻሜዉ ላይ የተሻለ ዉጤት እንደሚያመጡም ተስፋ ሰንቀዉ ዘቢደር አትሌቲክስ ክለብ በዞኑ መኖሩ በፕሮጀክት ታቅፈዉ ለሚለማመዱ ወጣቶች የተሻለ ቦታ ለመድረስ በከፍተኛ ሁኔታ አጋዥ እንደሆነም አስታዉቀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።