የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

=======================

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በቆጠር ገድራና አካባቢው የሚገኙ ተወላጅ ባለሀብቶችና ማህበረሰቡ በትምህርቱ ዘርፍ እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ለሌሎችም አካባቢዎች መነሳሳትን እየፈጠረ ይገኛል ።
የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶች ፡ በውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ የቀድሞ ተማሪዎችና ማህበረሰቡ በቆጠር ገድራ 2ኛ ደረጃ ት/ት ፡ የሻመነ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የቆጠር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በርካታ ስራዎች እያከናወኑ መሆኑን በአካል መመልከት ይቻላል ።
በ3ቱም ትምህርት ቤቶች ከ20ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ ተጨማሪ የመማሪያ ግንባታዎች ፡ የመምህራን መኖሪያ ቤቶች ግንባት ፡ የመማሪያ ክፍሎች እድሳት ፡ ውብና ማራኪ የሆኑ መግቢያ በር ግንባታ የላይበረሪ እና ሌሎችም ለትምህርት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንዲሟሉ በማድረግ ለተማሪዎች ምቹ የትምህርት አካባቢ እንዲፈጠርላቸው አድርገዋል።
የአካባቢው ተወላጆች ለረጅም አመታት የተለያዩ የልማት ስራዎች በተደራጀ መንገድ ከወረዳው መንግስት ጋር በመናበብ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለሌሎችም አካባቢዎች መነቃቃት በመፍጠር እንደ ወረዳው አሻራቸው እየጣሉም ይገኛሉ ።
እዣ ወረዳ እነደዚህ አይነት የልማት ተሳትፎ የሚደርጉ ትውልዶች በአሁን ሰዓት በሰፊው በመንቀሳቀስ በቅርቡ ምናውቀው እንደ ” ጋበር ” ያለ ለህዝብና ለነገ ትውልድ አሳቢ ድርጅት ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ታምር የሚመስሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን እጅግ ይበል የሚያሰኝ ነው ።
የእዣ ወረዳ አስተዳደር እነዚህን አካላት መጥተው አካባቢያቸው እንዲደግፉ በማወያየትም ይሁን ተቀራርቦ በመነጋገር እና ለሚቸግራቸው ጉዳዮች የመፍትሄ አካል እንዲሆን እያደረገላቸው ያለው ትብብር ይበልጥ ለማህበረሰባቸው እንዲያስቡ መነሳሳት እንደፈጠረላቸውም ተወላጅ ባለሀብቶቹ በተለያየ ወቅት በሚኖሩ መድረኮች ላይ በአስተያየት ሲገልፁ መረዳት ይቻላል።
በአጠቃላይ ከተቀናጁ ፡ ከተወያዩ ፡ በጋራ ጉዳዮች ላይ መግባባቶች ከተፈጡሩ ማህበረሰቡ በቀላሉ ከድህነት ከማውጣት በተጨማሪ ነገን አካባቢው ሚለውጥ ፡ ሀገርን ሚያሳድግ ትውልድ ጭምር ማፍራት ይቻላልና በቆጠርገድራ ቀበሌና አካባቢው የሚገኙ ተወላጅ ባለሀብቶች ፡ የቀድሞ ተማሪዎችና መላው ማህበረሰቡ የልማት ተሳትፎ በሁሉም የወረዳችንና ከተማ አስተዳደሩ አካባቢዎች በማሳፋፋት ታሪክ እንስራ መልዕክታችን ነው ። መረጃው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።