የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

=====================

ህዳር 25/2016 ዓም
በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ምክርቤት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የቀበሌ ምክር ቤቶች ፡ ስራስኪያጆችና የተቋሙ ግንባር ቀደም ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት አበረከተ።
ም/ቤቱ የ2016 ዓም 1ኛ ሩብ ዓመት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 34ኛ የቀበሌዎች ም/ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ/ፎረም / በዛሬው እለት አካሂዷል ።
የእዣ ወረዳ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሙከረም በደዊ በመክፈቻ ንግግራቸው በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የክትትልና ቁጥጥር አቅማቸው በማሳደግ የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ መስራት ይገባቸዋል ብለዋል ።
በቀበሌ ደረጃ አስፈፃሚ ሴክተሮች ስራቸው በምክር ቤት እያስገመገመ ያለበት አግባብ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተቀአፉ የመጡበት አግባብ መጠናከር እንደሚገባውውም አፈ ጉባኤው ጨምረው ገልፀዋል ።
አሁንም በትኩረት መሰራት የሚገባቸው የቀበሌ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የክትትልና ቁጥጥር ተግባር ስራ የሚጠይቅ መሆኑን ፡ የምክር ቤት ጉባኤ የሚያቆራርጡ ቀበሌዎች መኖራቸውና ሌሎች ትኩረት መሰጠቶ ያለባቸው ስራዎች በማረም የቀበሌ ምክር ቤቶች የህዝብ ውክልናቸው ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም አቶ ሙከረም ጨምረው አስገንዝበዋል።
የቀበሌ ምክር ቤት ተግባራት የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ሙከረም ህዝቡን የጣለባቸዉን አደራ ለመወጣት የሚያጋጥማቸዉ ችግሮችን በመለየት በቀበሌዉ ለሚፈለጉ ልማቶች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ እንዳለባቸዉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምክር ቤቱ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ካሳ የተለያዩ ሰነዶች ባቀረቡበት ወቅት እንደዚህ አይነት የምክክር መድረኮች በቀበሌ ደረጃ የሚገኙ ምክር ቤቶች ካላባቸው ጉድለት በማላቀቅና ልምድ በመቅሰም ለወከላቸው ማህበረሰብ በተገቢው ለማገልገልና በቁርጠኝነት ለመስራት እንደሚያስችል እንደሆነም አመላክተዋል ።
ም/ቤቶች የህዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ ዋና አላማ በማድረግ የተመሰረቱ መሆናቸዉን ጨምረው የገለፁቶ አቶ ተስፋዬ ይህንኑ በመገንዘብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ፣የሚጋጥማቸዉን ችግሮችን በመለየት፣ጉባኤዎችን በወቅቱ በማከናወን፣ በየቀበሌው ህዝቡ የሚፈልገዉን ልማት የሚያገኝበት መንገዶች በመዘርጋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰሩበት እንደሚገባም አመላክተዋል ።
ም/ቤቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የቀበሌ ምክር ቤቶች ፡ ስራስኪያጆችና የተቋሙ ግንባርቀደም ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።