ገዢ ትርክት

=======================

ገዢ ትርክት አንድነቷን የጠበቀች አገር ለመገንባት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ በእጅጉ የሚያስፈልግ በመሆኑ የጋራ እሳቤዎቻችንን በማጉላት ሀገራችን ለማበልፀግ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይገባል !!
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል መርህ 3ኛ ቀኑን የያዘው የሲቭል ሰርቫንቱ ስልጠና ሀገራዊ ገዢ ትርክት በሚል ርዕስ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።
ሰነዱን ያቀረቡት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሸምሱ አክመል ትርክት ማለት የአንድ ማህበረሰብ የወል ማንነት ለመግለፅ የሚያስፈልጉ የተሰነዱ እና በማህበረሰቡ ምግባር በሰፊው ተቀባይነት ያገኙ ታሪካዊ ክስተቶች ፡ ቁሳዊና ኢ -ቁሳዊ ትሩፋቶችና እሴቶች ማለት እንደ ሆነ አመላክተዋል ።
አብሮነትን በማጠናከርና ሰላማዊ መስተጋብርን ለመፍጠር ትርክት እና ስነ-ምግባር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው በሰነዱ አቶ ሸምሱ አመላክተዋል ።
ትርክት አዎንታዊና አሉታዊ በሚል ሁለት ገፅታዎች ያሉት ሲሆን ነጠላ እና ገዢ ትርከት በሚል በሁለት የሚከፈል እንደሆነም በሰነድ በማብራራት ከነጠላ ትርክ ይልቅ ገዢ ትርክት ለሀገር አብሮነትና አድነት መሰረት ሆኖ የሚያገለግል መሆኑንም ተገልጿል ።
በአጠቃላይ ገዢ ትርክት አንድነቷን የጠበቀች አገር ለመገንባት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ በእጅጉ የሚያስፈልግ በመሆኑ የጋራ እሳቤዎቻችንን በማጉላት ሀገራችን ለማበልፀግ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባ ተመላክቷል ።
የቀድሞ መጥፎ የሆኑ ታሪኮች ብቻ ነጥሎ በማውጣት ዛሬን አንድ እንዳንሆንና በሰላም እንዳንኖር የሚደጉት የፖለቲካ ሸፍጦች በመለየት የበለፀገች ሀገር ለመገንባት ፐብሊክ ሰርቫንቱ የድርሻውን መወጣት ይገባል።
ብሄራዊነት ሀገራዊ አንድነት ሳይሸረሽር የጋራ አላማዎችን የሚያጠናክር በመሆኑ ብልፅግና ፓርቲም ብሄራዊነትን ገዢ ትርክት በማድረግ በሁለንተናዊ መልኩ ያደገች ሀገር ለመገንባት አንግቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም በሰነዱ ተገልፆአል።
ይህን ሰነድ መነሻ በማድረግ በ3ቱም ቡድኖች ሰፊ ውይይት እየተደረገ ይገኛል ።

ያለንን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሲቭል ሰርቫንቱ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ።

ያለንን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሲቭል ሰርቫንቱ የድርሻውን መጣት እንዳለበት ተገለፀ።
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል ሀሳብ በዛሬው እለት በሀብት አስተዳደር መፍጠርና አጠቃቀም ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
የስልጠናው ሰነዱ ያቀረቡት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድራህማን ሀሰን እንደገለፁት ሁሉም በተሰማራበት ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም እራሳን ብሎም ሀገራችን መቀየር አለበት ።
በተለይም የጊዜ ታካኪነት በትላንት ወይም በዛሬ ብቻ ባለማሳበብ ለምን ይህ ሆነ ብሎ በማሰላሰል ከችግሮቻችን ተምረን አመለካከት በአንድ ጀንበር እንደማይቀየር በመገንዘብ ሀገር ማሳደግ እንደሚገባም በሰነዱ አመላክተዋል ።
በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አንድነት የዜጎች ክብር በማስጠበቅ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ በሰነዱ የተመላከተ ሲሆን የብልፅግና ማማ የደረሱ ሀገሮች ዋናው ሚስጥራቸው በትንሹ ሳይረኩ ጊዜን በአግባቡ ተጠቅመው ሌት ተቀን በልፋታቸው እዚህ መድረሳቸው መረዳት አለብንም ብለዋል ።
የትውልድ ሀብትና የብሄራዊ ሀብት እንዳይባክን እንዲሁም ሀብት ለመፍጠር የሚገጥሙ ተግዳሮቶች በመለትና መፍትሄ በማበጀት ወደ ተግባር ከመግባት አንፃር የብልፅግና ፓርቲ አመራርና አባላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎች መኖራቸውንም ተገልጿል።
ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሽለጋ ምራኒ ፡ /ሮ ሙሉ ስፍር እና ወ/ሮ ዙርያሽ ሀይሌ በሰጡት አስተያየትም በየቦታው በእጃችን ያሉ ሀብቶች የራሳችን አድርገን አስተሳሰባችን በማጎልበት ሰርተን የኑሮ ውድነት መቀነስ ይገባናልም ብለዋል ።
በተለይም እንደ ወረዳው መልማት ሲገባቸው ያለሙ እና በባህር ዛፍ የተሸፈኑ መሬቶች ከታካኪነት አስተሳሰብ ወጥተን በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ሁሉም ፐብሊክ ሰርቫንቱ በያለበትና በሚችለው አቅም መስራትና ማስተባበር እንደሚገባም አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረው ገልፀዋል ።
በእለቱም በ3ቡድኖች የተነሱት አስተያየቶችና ጥያቄዎች በየቡድኑ አወያዩች ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል ነው ።