



በጉራጌ ሀገረ-ስብከት እዣ የአገና ቅ/ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲህ ባማረ መልኩ እየተከበረ ይገኛል ።




በጉራጌ ሀገረ-ስብከት እዣ የአገና ቅ/ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲህ ባማረ መልኩ እየተከበረ ይገኛል ።






የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል
ታምረኛው ፡ እጅግ ጥንታዊ ፡ ታሪካዊና እድሜ ጠገብ ቅርሶች ባለቤት የሆነውን በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን የተመሰረተው የትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል ” የደቡብ ቁልቢ ” ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ !!
እዣ ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ ለቱሪስት ቀልብ የሚስቡ መስህቦች መገኛ ከሆኑት አካባቢዎች ውስጥ በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስትሆን እጅግ ማራኪና የአየር ንብረ ለውጥ ለመከላከል የሚያስችሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ደኖች ፡ ውብና ማራኪ ፏፏቴዎች ፡ ትክል ድንጋዮች ፡ ጥንታዊና በውስጣቸው እድሜ ጠገብ ቅርሶችን የያዙ ገዳማት ፡ መስጂዶች እና ካቴድሪያሎች ተጠቃሾች ናቸው ።
ከነዚህም መካከል እጅግ ታሪካዊ ፡ ጥንታዊና የሀገር ውስጥና የውጭ የጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ ያለው የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል “የደቡብ ቁልቢ ” ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ ።
የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ገደብ ቀበሌ የገረሙጀ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከዞናችን ዋና ከተማ ወልቂጤ በ52 ኪ ሜ እና የእዣ ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችው አገና በ10 ኪሜ ርቀት በስተ-ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ነው።
ካቴድሪያሉ በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን በስደት ከአክሱም ፂዮን “ወሰናይ ” ተብለው ይጠሩ በነበሩት አባት ከብዙ በጉዞአቸው ላይ ከነበረው ከድቅና ብዙ ታዓምር በኋላ ይዘው በማምጣት እንደሰየሙት በጉራጌ ሀገረ-ስብከት የእዣ ወረዳ ቤተ-ክህነት ስራስኪያጅ እና የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ብርሃን ብስራት አካለ ወልድ ይናገራሉ ።
በየ ዓመቱ ጥር 18 በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በመሳተፍ በድምቀት የሚከበረው ካቴድሪያሉ በአባታችን በአቡነ መልከ-ፄዲቅ ከተለያየ ቦታ በመምጣት እጅግ ቁጥር ያላቸው እንግዶች በክብረ -በዓሉ መገኘትና የተሳሉትን ስለት ቶሎ የሚሰማ መሆኑን ብዙዎቹ በመመስከራቸው ምክንያት ” የደቡብ ቁልቢ ” የሚል ስያሜ እንደሰጡትም የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ብርሀን ብስራት አካለወልድ ያስረዳሉ ።
በካቴድሪያሉ ከነሀስና ብር የተሰሩ ጥንታዊ መስቀሎች ፡ ፅዋዎች ፡ የተለያዩና እድሜ ጠገብ የብራና መፅሀፎች ፡ የጥበቃ መሳሪያዎችና በርካታ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞ ሀገርመሪ በነበሩ እንደ አፄ ሚኒሊክ ፡ ደጅ አዝማች ፡ ደጅ አዝማች ባልቻ ፡ ደጅ አዝማች ሀብተ -ጊዮርጊስ የተበረከቱ ቅርሶች በካቴድሪያሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰራው ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ መመልከት ወይም መጎብኘት ይቻላል ።
ካቴድሪያሉ ከሀይማኖት ስርዓት በተጨማሪ ከእምነቱ ተከታዮች ውጪ ያሉትም ጨምሮ በተለያየ ማህበራዊ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በደንና አካባቢ ጥበቃ ስራ አሻራ እያኖረ ያለና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ 22 ወገኖች በቋሚነትም ይረዳል ።
በየዓመቱ ጥር 18 እጅግ በአስደናቂ ሁኔታ የሚከበረው የአትፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በወረዳው የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር በማድረግና የገቢ አቅም በማሳደግ ረገድ የራሱ ድርሻ እንዳለውም የሚታመን ነው ።
ይህን ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮዓዊ እና የበርካታ ቅርስ ባለቤት የሆነውን ካቴድሪያል እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ።



=============================
“አንትሮሽት” የጉራጌ የእናቶች በዓል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ በቀጣነ ቀበሌ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።
“አንትሮሽት” እናቶች ለትውልድ ቀጣይነትና ለሀገር ስልጣኔ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ትልቅ በመሆኑ ውለታቸውን ለማስታውስ፣ ክብር ለመስጠትና ለማመስገን የሚደረግ ክብረ በዓል ነው።
ይህም በዓል የሚከበርላቸው እናቶች እድሜ ጠገብ የሆኑ የልጅ ልጅ ያዩ እናቶች ቤት የሚከበር ሲሆን ዕለቱ ግን ሁሉም እናቶች ያካተተ በዓል ነው፡፡
ይህ የእናቶች ቀን በሀገር አቀፍ የሁሉም በዓል እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ በአለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይ ለማስተዋወቅ በትኩረት መሰራት ይኖርበታል።
ዝርዝሩን እናደርሳለን ይጠብቁን !!






©2023. የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከአገና ኮንስትራክሽን እና ኢደስትሪያል ኮሌጅ ጋር በመተባበር. All Rights Reserved.