



በጉራጌ ዞን የእናቶች ቀን (አንትሮሽት) በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የእናቶች ቀን (አንትሮሽት) በየዓመቱ በጥር ወር እናቶች ለትውልድ ቀጣይነት፣ ለሀገር ሰላምና ልማት መረጋገጥ ላበረከቱት ወደር የሌለው አስተዋጽኦዋቸው ከስራ ነጻ ሆነው በባሎቻቸውና በልጆቻቸው የተለያዩ ስጦታ በማበርከት እንክብካቤ ይደረግላቸዋል።
አንትሮሽት በጉራጌ ብሄረሰብ ዘንድ ፈረንጆች “ማዘር ዴይ” ብለው እንደሚያከብሩት ለረጅም ዘመናት ሲከበር እንደነበር የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በፕሮግራሙ የክልል፣ የጉራጌ ዞን፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን፣ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኦቢኤን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ እናቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጉመር ወረዳ አበኬ ቀበሌ ላይ እየተከበረ ይገኛል።



