
============================
በዘንድሮ መኸር ወቅት በዋና ዋና ሰብሎች 9129.5 ሄ/ር መሬት በማልማት 853ሺህ 950 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሏል እየተሰራ መሆኑን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ፅ/ቤቱ የ2016/17 ምርት ዘመን የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።
በእለቱም መድኩን የመረቱ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደገለፁት የግብርናው ዘርፍ እንደ ሀገር የሚደረገው ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር የማይተካ ሚና አለው ።
ግብርናው የምግብ ዋስትናን ለማወጋገጥ እንዲሁም እንደ ሀገር የገጠመውን የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለመዋጋትና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የዳበረ ኢኮኖሚ ለመገንባት አይተኬ ሚና አለው ያሉት ሀላፊዋ አርሶአደሩ አመለካከት መለወጥ ሚቻለው ሙያተኛው በቁርጠኝነት መስራት ሲችሉ መሆኑን ተገንዝቦ በሁሉም የግብርና ዘርፎች የአርሶአደሩ የማምረት አቅሙ እንዲጨምር መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ከምናመርትበት አካሄድ በአመት ከ3 ጊዜ በላይ ማምረት የምንችልበት የተለያዩ ሀገራዊ መነሳሳቶች ተቀርፀው ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ተገብቷል ያሉት ወ/ሮ ትብለጥ እንደ ወረዳውን ይህንን ግብ መሳካት እንዲቻል በተለይም አመራሩና ባለሙያው ከወትሮ በተለየ ድጋፍ ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ ይገባልም ብለዋል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው እንደ ሀገር ከተረጂነት ተላቀን ወደ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ የመገንባት ግባችን ለማሳካት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል ።
እንደ ወረዳው በዘንድሮ ዓመት በትኩረት መምራት የተጀመሩ ያልታረሱ መሬቶች በስፋት የማረስ ፡ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ፡ ለምግብ ዋስትና ቁልፍ ሚና ሚጫወተው የእንሰት ልማት ስራ በስፋት የማልማትና በሽታን የመከላከል አፅዕኖት ተሰርቶት እንደሚሰራም ዋና አስተዳዳሪው አመላክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ እንደ ወረዳው ግብርናው በይበልጥ እንዲሻሻል ማነቆ ሆነው የተለየትን ጉለቶች በማረም የቡና ልማት ስራዎች ፡ የስራስርና የአዝዕርት ልማት እንዲሁም የአትክልት ስራዎች ፡ የሌማት ትሩፋት እና የአረንጓዴ አሻራ ልማት ልዩ ትርጉምና ትኩረት ይሻሉ ያሉት አቶ ዘውዱ ይህንኑ እውን ለማድረግ ከአመራር ጀምሮ እስከ አምራች አርሶአደር ድረስ በዚህ መኸር ልዩ ትኩረት መስጠትና ጠንካራ የማስፈፀም አቅም በመገንባት በሂደቱም በርካታ የስራ እድል በመፍጠር የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ ሃላፊነታችን በአግባቡ መወጣት ይገባናልም ብለዋል ።
የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በ2016 በጀት ዓመት በእስካሁን ሂደት ዋና ዋና ወቅታዊ የግብርና ስራዎች ሰፊ ርብርብ በማድረግ ግብርናው ላይ ያሉት ማነቆዎችን ለመፍታት በርካታ ተግባራት የተፈፀመ ሲሆን በቀጣይም በመኸር እርሻ ሰፊ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ።
በወረዳው በዘንድሮ መኸር ወቅት በአዝዕርት ፡ በፍራፍሬ ፡ በሆልቲከልቸር ሰብሎች 9129.5 ሄ/ር መሬት በማልማት 853ሺህ 950 ኩንታል ምርት ለማልማት ግብ ተጥሏል ያሉት ሀላፊ በዚህም ከ10 ሺህ በላይ አርሶአደሮች ተሳታፊም ይሆናሉ ብለዋል ።
የደንና አግሮፎረስተሪ ችግኝ ተከላ 9.5 ሚሊየን ችግኞችን የሚተከሉ ሲሆን ሌሎችም በርካታ የግብርና ልማት ስራዎች በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ እንዲከናወኑ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም የገለፁት አቶ መቻል ይህንኑ በሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየትም በሁሉም ቀበሌዎች የተለዩት አርሶአደሩን በአግባቡ ያለማስጠቀም ጉለቶች እንዲታረሙ በባለቤትነት በመውሰድ የአርሶአደሩ ምርትና ማርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።




