



ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም
ጋበር የበጎ አድራጎት ድርጅት ከእዣ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት እና ከአገና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በ2016 በጀት ዓመት 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረግ አካሄደ!!
በዕለቱ የግንዛቤ መፍጠሪያና መወያያ ሰነድ በዶ/ር ደርብ የቀረበ ሲሆን የአገና ፖሊ-ቴክኒክ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ ኮሌጁ የደረጃ-5 ስልጠና ፈቃድ ያገኘባቸው ሙያዎችና አጠቃላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ ተመራጭነት ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመድረኩ 720 ተማሪዎች: የጋበር-በጎ አድራጎት ድርጅት አመራሮች: የእዣ ወረዳና አገና ከተማ አመራሮች እንዲሁም የአገና ፖሊ-ቴክኒክ ዲንዎች ተገኝተው ውይይት አድርገዋል።
በዕለቱ የተገኙት የጋበር በጎ-አድራጎት ድርጅት ቦርድ አመራሮች(አቶ ታምሩ ማኒ: አቶ ጤናዬ ጠንክር እና አቶ ባንሸቢ ቴዦ) እንዲሁም የእዣ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊና ም/አስተዳዳሪ አቶ ተጠምቀ በርጋ አብዛኛው ተማሪ የኮሌጅ መግቢያ ነጥብ ያሟላ በመሆኑ ዘመኑ የቴክኖሎጂና የሙያ ክህሎት መሆኑን በመገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጊዜያቸው ሳያባክኑ ወደ ኮሌጅ ገብቶ በመመዝገብ በተለያዩ አማራጮች ስልጠናዎችን በመከታተል የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ በጥብቅ አሳስበዋል።አስተያየት ሰጪ ተማሪዎች በበኩላቸው የኮሌጅ ስልጠና ተመራጭ መንገድ እንጂ አማራጭ አለመሆኑን እንዲሁም ዩኒቨርስቲ የገቡትም ቢሆን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሙያ መሰልጠን እንደሚገባቸው ጭምር አብራርተዋል።
በዕለቱም 12ኛ ክፍል ላጠናቀቁ ሴት ተማሪዎች የኮሌጅና የዩንቨርሲቲ ስልጠናቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ለ1 ዓመት ከግማሽ የሚጠቅም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።በመጨረሻም ጋበር በጎ-አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ሽልማትና በመድረኩ ለተሳተፉ ተማሪዎች የተለያዩ ወጪዎችን በመሸፈን ተጠናቋል።







