በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የ2016 ዓም የትምህርት ጉባኤ ተካሄደ ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የ2016 ዓም የትምህርት ጉባኤ ተካሄደ ።

በጉባኤውም የ2016 በጀት ዓመት እና የ2017 የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ፡ የ2017 ዋና ዋና ግብ እቅድ ላይ ውይይት ማድረግና በ2016 የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ፡ በ2016 የተሻለ አስተዋፅኦ ያደረጉ ድርጅቶች ፡ ማህበር እና አካላት እንዲሁም ተቋማት የእውቅናና ማበረታቻ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

በውይይቱ የእዣ ወረዳ አመራሮች ፡ ርዕሰ መምህራን ፡ ስራስኪያጅ ፡ ሊቀመናብርት ፡ የወመህ ሰብሳቢ እንዲሁም ተሸላሚ ተማሪዎችና የፅ/ቤቱ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ዝርዝሩ ተከታትለን እናደርሳለን !!

የ2017 ዓም የ1ኛ ሩብ ዓመት 4ኛ ዙር 12ኛ አመት 44ኛ መደበኛ ጉባኤ አካሂዷል

እንደ ወረዳው የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በማጠናከር ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ምክር ቤት አስታወቀ ።

ም/ቤቱ የ2017 ዓም የ1ኛ ሩብ ዓመት 4ኛ ዙር 12ኛ አመት 44ኛ መደበኛ ጉባኤ አካሂዷል ።

የእዣ ወረዳ ምክርቤት ም/ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰናይት ሳህሌ በመግቢያ ንግግራቸው እንደተናገሩት ሀገራችን የጀመረችው የእድገት ጎዳና ተጠናክሮ እንዲቀጥል በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች የክትትልና ቁጥጥር ስራ በማከናወን ሚናቸው የጎላ ነው ።

በኢኮኖሚው ዘርፍ በግብርና ምርት ላይ ሙሉ ቴክኖሎጂ በመጠቀም እንደ ሀገር የተጀመረው ድል በወረዳውም ላይ በእርሻ ካላንደር መሰረት ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የምግብ ሉአላዊነት ያረጋገጠ አርሶአደር መፍጠር እንደሚጠበቅም ም/አፈ-ጉባኤዋ ጨምረው ተናግረዋል።

በጤናው ዘርፍም እየተሰጠ የሚገኘው የጤና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በማጠናከር በተለይም በወባ ወረርሽኝ ላይ እንደ ወረዳው እየተሰራ ያለው የመከላከል ስራ ማጠናከር አለባቸው ያሉት ወ/ሰናይት በትምህርት ዘርፍም እንደ ሀገር የገጠመው የውጤት ስብራት ለመካስ ሁሉም መረባረብ እንደሚያስልግም ገልፀዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ የ2017 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም የግብርናው ዘርፍ የሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገትና ድህነት በመቀነስ ረገድ ባለው ወሳኝ ድርሻ ምክንያት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በ2016/17 ምርት ዘመን በመኸር ወቅት በአዝዕርት ሰብሎች 9991 አርሶአደሮች በማሳተፍ 6570 ሄክታር መሬት ለማልማት መቻሉንም አመላክተዋል።

በወረዳው ለዘመናት ያልታረሱ መሬቶች እንዲለሙ ሰፊ ጥረት የተደረገ ሲሆን በበልግና መኸር እርሻ 931.5 ሄክታር መልማቱን ጨምረው የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው በፍራፍሬ ልማት በጠቅላላው 111ሺህ 450 ያህል ተተክለው አስፈላጊውን የመንከባከብ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በትምህርት ዘርፍ የተለያዩ የንቅናቄ መድረክና የትምህርት አመራር ሪፎርማ የማድረግ ስራ የተሰራ ሲሆን በ2017 የተማሪዎች ቅበላ ከ1- 12ኛ ክፍል 13ሺህ 921 ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸው እተከታተሉ ይገኛሉ ያሉት አቶ ዘውዱ የመማር ማስተማር ስርዓት ምቹ ለማድረግ በጀት ወሳኝ በመሆኑ ከህብረተሰቡ ተሳትፎ ባሻገር በወረዳው መንግስት 4ሚሊየን 500 ሺህ ብር ድጋፍ መደረጉንም ጠቁመዋል ።በወረዳው በተያዘው አመት አስከፊ እየሆነ የመጣው የወባ በሽታን ጫና ለመከላከል በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በሁለት ሳምንት ከተመረመሩ 1601 ሰዎች መካከል 495 ሰዎች የወባ ህመም ተጠቂ ሆነው አስፈላጊውን ህክምና እንዲያደርጉ መደረጉን የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪው ከዚህ በተጨማሪ በተቋሙ ወቅታዊ የሆኑ ክትባት የመስጠትና የእናቶችና ህፃና ሞት መቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።

በክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ15 የስራ መስኮች 29 ሺ 566 ወጣቶች በማሳተፍ 49ሺህ 170 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሰፊ ጥረት ተደርጎአል ያሉት አቶ ዘውዱ ይህም በመንግስትና በህብረተሰብ ይወጣ የነበረው 16 ሚሊየን 970 ሺህ 600 ብር ማዳን ተችሏልም ብለዋል።

በአጠቃላይ እንደ ወረዳው በሩብ አመቱ በሁሉም ተቋማት የታቀዱ ስራዎች ለማከናወን ሰፊ ጥረት መደረጉን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው በቀጣይ ምክር ቤቱ በጉለት ያነሳቸው ተግባራቶች የባለሙያና አመራር ተሳትፎ በማጠናከር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም አብራርተዋል።

በምክር ቤቱ አባላት የተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሚመለከታቸው ተቋማት ሀላፊዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ቀጣይ ሊታረሙ በሚያስችል አኳኋን ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ ወ/ሮ አሰለፈች ክብሩ የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናትፅ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም አቶ ሲሳይ ክፈተው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው አማካሪ እንዲሆኑ በብልፅግና ፓርቲ የቀረበው ሹመት መርምሮ አፅድቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በግብርና ልማት ፅ/ቤት አስተባባሪነት የመስክ እየተካሄደ ይገኛል

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በግብርና ልማት ፅ/ቤት አስተባባሪነት የመስክ እየተካሄደ ይገኛል።

በወረዳው ሸህረሞ ፡ ቦዠባር ፡ አንበሊና የስራይ ቀበሌዎች ላይ የገብስ ፡ የጤፍ ፡ የፍራፍሬና የነጭሽንኩርት ማሳዎች ጉብኝት እንደሚደረግም ተጠቁሟል ።

በጉብኝቱም የወረዳው አመራሮች ፡ የወረዳና ቀበሌ ባለሙያዎች ፡ የቀበሌ ሊቀመናብርትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ናቸው ።

ዝርዝሩ ተከታትለን የምናደርስ ይሆናል።