የእዣ ወረዳ ስፖርት ምክር ቤት የ2017 ዓም ጉባኤ አካሂዷል።

የስፖርት ዘርፉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አስታወቀ ።

ህዳር 30/2017 ዓም

የእዣ ወረዳ ስፖርት ምክር ቤት የ2017 ዓም ጉባኤ አካሂዷል።

በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት የስፖርት ልማቱ በማሳደግና በዘርፉ አቅምን በመጠቀም ህብረተሰቡ በስፖርቱ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።

ስፖርት ለኢኮኖሚ እድገትና የህዝቡ አንድነትን የበለጠ ለማጠናከር ጉልህ ሚና ይጫወታል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ዘርፉም ለማሳደግ በትምህርት ቤቶች፡ በታዳጊ ፕሮጀክቶች፡ ከግል ተቋማት እና ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

ዘርፉ ይበልጥ ለማሳደግ የማዘውተርያ ስፍራዎች እንደበራከቱ ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ዘውዱ ከዚህ በተጨማሪ ከተለያዩ አካላት ሀብትን በአግባቡ በመሰብሰብ በ2016 ዓም አፈፃፀም ላይ የታዩት ጉለቶችን በማረም ውጤታማ ስራ መስራት ይገባልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ ነሪ በበኩላቸው የስፖርት ልማት እድገት በተሻለ መልኩ የህዝባችና ሀገራችን ጥቅምና ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ መምራትና ወደ ተሻለ እድገት ማሻገር ያስፈልጋል።

ሀላፊው አክለውም ስፖርት ከልማቱ በተጨማሪ ዜጎች እርስ በርስ በማቀራረብ የተረጋጋና ሰላማዊ ማህበረሰብ በመፍጠር በዘርፉ የሚገኘው ጥቅም ብዙ እንደሆነ በመረዳት በረዳው በ2016 በጀት ዓመት በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ብለዋል ።

በአመቱ የት/ት ቤቶች ውድድር ፡ የክላስተር ውድድር ፡ የወረዳና የዞን ልዩ ልዩ ሻንፒዮና የተደረጉ ቢሆንም በዘርፉ የሚጠበቀው ውጤት አንፃር ጉለት ያለበት ነው ያሉት አቶ ፍቅሬ በቀጣይ ይህንኑ ባረመ መልኩ የተለያዩ ባለድርሻ አካል በማሳተፍ የተሻለ ስራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

የፅ/ቤቱ ም/ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ጠቅልል ትግስቱ የ2016 ዓም አፈፃፀምና የ2017እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ዘርፉ በይበልጥ ለማጠናከር ከሀብት አሰባሰብ ባለፈ ትምህርት ቤቶች የስፖርት መፈልፈያ ከመሆናቸው አንፃር ትኩረት የሚፈልግ በመሆናቸው በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።

በእለቱም ሰያ የቴኳንዶ ክለብ ሰልጣኞች የተለያዩ የስፖርት ትዕይንት ለተሳታፊው ያሳዩ ሲሆን በጉባኤው መጨረሻም እስፖርትን በመደገፍ የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት የማበረታቻ ሰርተፊኬት ሽልማት ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።