






የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ኢኮኖሚአዊና ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ ።
በእለቱም የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትግስት መንግስቱ እንደገለፁት ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር የተጋለጡትን የህብረተሰብ ክፍሎች በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት በመስጠት የእርስ በርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልና ልምዱን ማጠናከር ይገባል።
እንደ ወረዳው በተለያየ ችግር ምክንያት ድጋፍ የሚሹና አረጋውያንና ሌሎች በተለያ ችግር ውስጥ ሚገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳይዳረጉ አቅም በፈቀደው ደረጃ ለማቋቋምና ለመርዳት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ ያሉት ሀላፊዋ የማህበረሰቡ ባህልና ልምድ በማጠናከር በተለይም ቀጣይ የሚከበረውን የገና በዓል ላይ የዕምነቱ ተከታይ ሲያከብር በየአካባቢው ለነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም በፈቀደ መልኩ ያለው ለሌለውን በማካፈል ድጋፍና እንክብካቤ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት አሳስበዋል ።
በዛሬው እለትም ድጋፉ የተደረገው በወረዳው ከሚገኙ ቀበሌዎች የተወጣጡ የድሃ -ድሃ ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሆን ለእያንዳንዳቸውም 2ሊትር ዘይት ፡ 10 ኪሎ ዱቄትና 5 ሳሙና ድጋፍ መደረጉን የገለፁት ወ/ሮ ትግስት ይህም ድጋ በሌላ ጊዜያቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ሁሉም ማህበረሰብ በየአካባቢው ችግርተኞችን ዘላቂነት ባለው መንገድ መርዳትና መደገፍ እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸውም አካላት ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።










