





በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአመራር ግምገማ መድረክ ተጠናቋል ።
የአመራር የግምገማ መድረክ የአመራሩን ችግሮች በመቅረፍ ፡ የኢትዮጵያን ህልም እውን ማድረግ ላይ ያለመ ስለመሆኑም ተመላክቷል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በግምገማው ማጠቃለያ ተገኝተው እንደገለፁት “ከቃል እስከ ባህል” ያሉብንን ችግሮችን በመቅረፍ እንደ ሀገር ብሎም ወረዳችንን ህልም እውን እናደርጋለን በሚል መሪ ሀሳብ የወረዳው ጠቅላላ የአመራር የግምገማ መድረክ ለሁለት ቀናት መካሄዱንም ጠቁመዋል።
የግመገማ መድረኩ ግለሰው ሳይሆን ስራውን ታይቶ የተመዘነ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ግምገማው በጥሩ ዲሲፕሊን የተመራ መሆኑንና ከህዝብ ተጠቃሚነት አንፃር የተመዘነ እንደነበርም አመላክተዋል።
በቀጣይም የፓርቲው ጠቅላላ አመራሮች የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን በማረም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንዳለበትም አቶ ዘውዱ አስገንዝበዋል።
የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው እንዳሉት አመራሩ እራሱን ያየበትና ችግሩን የተረዳበት ሂደት እጅግ አበረታች እንደነበረ ጠቁመው ቀጣይ የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነቱን በማጠናከር የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ለውጥ ላይ መትጋት ይገባልም ብለዋል።
ምዘናው አመራሩ እራሱን የፈተሸበትና ጉድለቱን የለየበት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንፃር የቀሩ ተግባራት በጥልቀት የገመገመበት መድረክ እንደነበርም ዋና የመንግስት ተጠሪው አመላክተዋል።
በቀጣይም አመራሩ የተግባርና የሃሳብ አንድነቱን በማስቀጠል የማህበረሰቡን ችግር ለይቶ በማቀድ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅበትም አቶ ተሾመ ተናግረዋል።
አንዳንድ አስተያየት የሰጡት አመራሮች እንዳሉት ምዘና እራሳቸውን በሚገባ ያዩበት መሆኑን ገልፀው በምዘናው የተለዩ ችግሮች በአጭር ጊዜ በማረም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲረባረቡም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ /ቤት ነው ።




