በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ቦዠባር ታዳጊ ማዘጋጃ 8 የመኖርያ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ ለተጫራቾች አቅርቧል።

=======በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ቦዠባር ታዳጊ ማዘጋጃ 8 የመኖርያ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ ለተጫራቾች አቅርቧል።

የጨረታው ሠነድ ሽያጭ ከቀን 14/05/2017 እስከ 27/05/2017 ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ጨረታው በቀን 28/05/2017 ከጠዋቱ 03:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

ማንኛውም ተጫራች ከቀን 14/05/2017 ጀምሮ ቦታውን ምልከታ ማድረግ የሚችል ይሆናል።

ማሳሰቢያ

አንድ ተጫራች ከአንድ ሰነድ ውጪ መግዛትና መወዳደር አይችልም።

የቅድመ ክፍያ ከ25% በላይ መሆን አለበት

CPO ማሰርያ መጠን ከ20% ማነስ የለበትም

ተቋሙ ጫረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

=======ጥር 13/2017 ዓ.ም

የጉራጌ ማህበረሰብ ነቖ የልጃገረዶች በዓል ቀን በማልማትና በማስተዋወቅ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ ጠየቁ።

ነቖ የልጃገረዶች በዓል ቀን በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በጉየና የስዋ ቀበሌ ዞናዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል።

ነቖ (ኧረቘ) በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ በጥር ወር ላይ ወይም ገና በዋለ እስከ 15ኛው ቀን ባሉት ጊዜያት በሴት ልጃገረዶች የሚዘወተር ባህላዊ በዓል ነው።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ እንዳሉት መምሪው ከዞኑ አስተዳደር እና በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የጉራጌ ማህበረሰብ የልጃገረዶች በዓል ነቖ ከማልማትና ከማስተዋወቅ ባሻገር የገቢ ምንጭ ለማድረግ እየሰራ ነው።

የጉራጌ ማህበረሰብ ከጥንት ጀምሮ ለሴቶች ይሰጠው ለነበረው ክብርና ዴሞክራሲያዊ አመለካከት ነቖ አና አንትሮሸት የመሳሰሉ ሁነቶች ማሳያዎች ናቸው ያሉት ወይዘሮ መሰረት መሰል እሴቶች በማልማትና በማስተዋወቅ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የነቖ በዓል ለማህበረሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ መሰረት ሴት ልጃገረዶች ነጻነታቸው በማወጅ ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክሩበት በዓል ነው ያሉት።

ለበዓሉ ከታህሳስ ወር ጀምሮ ቅድመ ዝግጅት እንደሚደረግ ያነሱት ኃላፊዋ ለዚህም ሴት ልጃገረዶች ቤት ለቤት እየዞሩ ከቤተሰብ እስከ አካባቢ ነዎሪዎች ገንዘብን ጨምሮ በአይነት የገብስ የአተር እና ሌሎች ስጦታዎች ተበርክቶላቸው በበአሉ መጨረሻ እየበሉና እየጠጡ እየጨፈሩ የሚደሰቱበት በዓል መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ ባህላዊ የልጃገረዶች በዓል ይዘቱን ተጠብቆ ለትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም አመላክተዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው የልጃገረዶች በዓል ባህላዊ እሴቱና ትውፊቱ ጠብቆ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ የወረዳው መንግስት ባለፉት አመታት ተቀዛቅዞ የነበረውን ይህ እሴት እንዲያንሰራራ በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ባህል የአንድን ማህበረሰብ ማህበራዊ፣ አስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚገለጽበት መሳሪያ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ የማህበረሰቡ ባህሎችን በተገቢው በመጠቀም በመንከባከብና በማሳደግ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

የወረዳው ባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የሺነሽ ተካ እንዳሉት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ነቖ ሴት ልጃገረዶች ነጻነታቸውን የሚያውጁበት፣ ደስታቸውን የሚገልጹበትና የእርስ በእርስ ማህበራዊ መስተጋብራቸውን የሚያጠናክሩበት በዓል ነው።

የጉራጌ ማህበረሰብ ነቖን ጨምሮ የበርካታ እሴቶች ባለቤት መሆኑ ያነሱት ኃላፊው እነዚህን ማህበራዊ መስተጋብርና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው መሰል እሴቶችን ከመጥፋት በመታደግ እንዲለሙና እንዲተዋወቁ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በበዓሉ የተሳታፉ ሴት ልጃገረዶች እናቶች በዓሉ ከተጋረጠበት መፋዘዝ ወጥቶ በድምቀት መከበሩ ደስታ እንደፈጠረባቸው ተናግሯል ።

በዓሉ እንዲያንሰራራ መንግስት ለሚደረገው ጥረት አመስግነው በቀጣይ እሴቱ እንዲለማና እንዲተዋወቅ በማድረግ እንዲሁም የማህበረሰቡ ማህራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያጎለብት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት እንዲሰሩም ጠይቀዋል።

ነቖ ወይንም የልጃገረዶች በዓል ቀን በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በጉየና የስዋ ቀበሌ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

=======ነቖ ወይንም የልጃገረዶች በዓል ቀን በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በጉየና የስዋ ቀበሌ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

ነቖ (ኧረቘ) በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ በጥር ወር ላይ ወይም ገና በዋለ እስከ 15ኛው ቀን ባሉት ጊዜያት በሴት ልጃገረዶች የሚዘወተር ባህላዊ የበዓል አይነት ነው።

በዓሉም ሴት ልጃገረዶች ነጻነታቸውን የሚያውጁበትና ደስታቸውን የሚገልጹበት በዓል ነው።

በበዓሉ ወቅት ልጃገረዶች ተሰባስበው በየቤቱ እየዞሩ ልክ እንደ አበባዮሽ በአይነትና ገንዘብ ይሰበስባሉ፣ ሁሉም የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችና ምግብ ከተዘጋጀ በኋላ ከአካባቢው በአንዷ ልጃገረድ ቤት በማደር የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት እየጨፈሩና እየበሉ ያድራሉ፡፡

የነቖ በዓል በጥር ወር የሚከበር ሲሆን ከታህሳስ ወር ጀምሮ ለበዓሉ የሚሆን ቅድመ ዝግጅት ተጀምሮ ክትፎ፣ ቆሎ፣ በሶ፣ ቦርዴና ሌሎችም ባህላዊ ምግቦች ዝግጅቶች ይደረጋል። ልጃገረዶቹ ከሚያደርጉት ዝግጅት ባለፈ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ወላጆቻቸው አስፈላጊውን እገዛ ያደርጉላቸዋል።

ይህ የልጃገረዶች በዓል በዞኑ በየአመቱ በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝና የዘንድሮ የነቖ የልጃገረዶች በዓል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር ወር መጨረሻ ድረስ በልዩ ድምቀት እየተከበረ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በበዓሉም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ፣ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ፣ የወረዳው ባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የሺነሽ ተካና ሌሎችም የዞንና የወረዳው የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።