*የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ*

የካቲት 11/2017 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2017 ዓ.ም የመምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር ምዘና፣ የቲቶሪያል ኦሮንቴሽንና ወቅታዊ ስራዎች በተመለከተ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻልና በዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመስራት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ሚናው የላቀ ነው።

የ2016 የመምህራን ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር የምዘና አፈጻጸም ግምገማ፣ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠው ቲቶሪያል አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ጥሩነሽ ምኑታ፣ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችና የሴቶች ክንፍ ኃላፊዎች፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የዞኑ የወላጅ መምህር ህብረትና የመምህራን ማህበር ተወካዮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

“መፍጠንና መፍጠር ለጉባኤያችን ስኬት “

“መፍጠንና መፍጠር ለጉባኤያችን ስኬት ” በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ በጉራጌ ዞን አገና ከተማ አስተዳደር ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩም የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ በፓርቲው የተገኙ ውጤቶች በማጠናከርና ችግሮችን በመለየት ብልጽግናን እውን ለማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተመላክቷል ።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ፈይሰል ሀሰን ፡ የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሀላፊ መስፍን ቴርገም ፡ የአገና ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ ፡ የአገና ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ከልል ክብሩ ፡ የከተማው አመራሮችና ነዋሪዎች ተሳታፊ ናቸው ።

ዝርዝር ይኖረናል ይከታተሉን !!

*ባጃጅ የሠራው የ14 ዓመት ታዳጊ*

=====ባጃጅ የሠራው የ14 ዓመት ታዳጊ

የ14 ዓመት ታዳጊና የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አብዱልሃፊዝ ጸጋዬ የሚኖረው በጉራጌ ዞን ሙኽር አክሊል ወረዳ ነው።

የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች የሠራው አብዱልሃፊዝ እስካሁን ወደ አምስት የሚጠጉ የፈጠራ ሥራዎች መሥራቱንም ገልጿል። ከእነዚህም ውስጥ በኤሌክትሪክ እና በፀሐይ ብርሃን የሚሰራ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ይገኝበታል።

ከቴክኖሎጂው ጋር የተዋወቀው የሰባት ዓመት ልጅ እያለ መሆኑን የሚገልጸው የፈጠራ ባለሙያው÷ የመብራት እና የመኪና ፈጠራ እጅግ እንደሚያስደስተው ተናግሯል።

ታዳጊው ወደ ፈጠራ ሥራ የተሳበው ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ መጠየቅ እና መመራመር ስለሚወድ መሆኑንም ይገልጻል።

የታዳጊው እህት አምሪያ ጸጋዬ የወንድሟን የፈጠራ ሥራዎችን በተመለከተ በሰጠችው አስተያየት የመጀመሪያ ሥራው የምግብ ማቅረቢያ ትሪን እንደመሪ በመጠቀም በእንጨት እና በሌሎች ቁሳቁስ መኪና መስራቱን ታስታውሳለች። ከዛ በኋላ ግን በተለያዩ የትምህርት ቤት ውድድሮች ላይ እየተሳተፈ ማሸነፍ መቻሉን ትናገራለች።

አብዱልሃፊዝ ወደ ፈጠራ ሥራዎች የገባው በአካባቢው ያሉ እናቶችን ችግር በመመልከት በተለይም እናቶች ወደ ጤና ተቋም ለመሄድ የሚገጥማቸውን ውጣ ውረድ በአቅሙ መፍትሄ ለመስጠት እንደሆነም ገልጿል።

ታዳጊው በፀሐይ ብርሃን የምትሄድ ባለሦስት እግር ወይም በተለምዶ ባጃጅ የምትባለውን ተሽከርካሪ፣ መለስተኛ አይሱዚ እና እሳት ማቀጣጠያ ከሠራቸው የፈጠራ ሥራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

አብዱልሃፊዝ በፈጠራ ሥራዎቹ ምክንያት በወረዳ እና ዞን ደረጃ በተደረጉ የተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

ወደ ፊት የሠራትን ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪውን ወደ ገበያ ለማውጣት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ድጋፍ እንዲደረግለትም ጠይቋል።

ታዳጊው የፈጠራ ሥራዎቹን በተመለከተ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ያደረገውን ቆይታ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይመልከቱ👇👇

ተቋማዊ አደረጃጀት በማጠናከርና አገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ህዝባችን የሚፈልገዉን ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።

=========ተቋማዊ አደረጃጀት በማጠናከርና አገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ህዝባችን የሚፈልገዉን ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ የማዕከል የብልፅግና ህብረት ፐብሊክ ሰርቫንት የአባላት መድረክ ተካሂዷል ።

በመድረኩም ተቋማዊ አደረጃጀት በማጠናከር የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ህዝባችን የሚፈልገዉን ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል ።

የህዝባችን ኢኮኖሚ ለማሻሻል ሁሉም ጠንክሮ በመስራት በቀላሉ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ከእራሱ አልፎ ለሀገር እድገት ከፍተኛ ለዉጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን በመድረኩ ውይይት ተደርጎበታል።

በአጠቃላይ እንደ ወረዳው በትምህርት ፡ በግብርና ፡ በጤና ፡ በስራ እድል ፈጠራ እና ሌሎችም በጥንካሬ የተከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራቶች በማስቀጠል በአፈፃፀም ወቅት የነበሩትን ጉለቶችን በማረም ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆን ሲቭል ሰርቫንት አባሉ የድርሻውን መወጣት ይገባዋልም ተብሏል።