


=====ህግን በማስከበር የንግዱ ስርዓት ፍትሃዊ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ቅንጅት የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።
የካቲት 17/2017 ዓም
በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ የህገ – ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይልና ባለድርሻ አካላት ውይይት አካሂደዋል።
የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት እንደ ወረዳው ብሎም እንደ ሀገር ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እና ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ።
ከነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እንዲሁም በሌሎችም ንግዶች ላይ የዋጋ ጭማሪ አንፃር እየተስተዋሉ ያሉ አዝማሚያዎችን በተገቢው በመፈተሽ ጠንካራ የቁጥጥር ስራ መስራት እንደሚገ ዋና የመንግስት ተጠሪው ጨምረው ተናግረዋል።
እንደ ወረዳው ከፀጥታው ዘርፍ ጋር በተቀናጀ መንገድ በህገ -ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ መደበኛ እና ድንገተኛ የክትትል ስራው ማስቀጠልም እንደሚገባም አቶ ተሾመ ጨምረው ተናግረዋል ።
የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በለጠ ሳህሌ በበኩላቸው ህግን በማስከበር የንግዱ ስርዓት ፍትሃዊ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ቅንጅት የበለጠ ማጠናከር ይገባልም ብለዋል።
የነዳጅና ኮንትሮባንድ ህገወጥ ተግባራት የሚፈፅሙ ነጋዴዎች ላይ በአዲሱ አዋጅ መሰረት አስተማሪ የሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰደም ሀላፊው አክለው ተናግረዋል ።
በቀጣይ በተለይም ማደያ በሌለባቸዉ አካባቢዎች የነዳጅ ችርቻሮ ፈቃድ የተሰጣቸዉ ቸርቻሪ ነጋዴዎች የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ክትትል ማድረግ ላይ በትኩረት ይሰራል ያሉት አቶ በለጠ በሌሎችም ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ግብረ ሀይሉና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይገባቸዋልም ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት እንደ ወረዳው ከህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ስራዎች በቀጣይ ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።




