በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለተከታታይ 25 ቀናት በተከናወነው የ2017 ዓም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተግባር 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተለያዩ ስትራክቸሮች መልማቱን ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለተከታታይ 25 ቀናት በተከናወነው የ2017 ዓም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተግባር 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተለያዩ ስትራክቸሮች መልማቱን ተገለፀ።

የ2017 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ መዝግያ ፕሮግራም በወረዳው በኮኬራ ቀበሌ ኖርቻ ንዑስ ተፋሰስ ተካሂዷል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በመዝጊያው ፕሮግራም ወቅት እንደገለፁት የዘንድሮው ተፋሰስ ልማት ስራ መላው የወረዳው ህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ የተሳተፉበት መሆኑን ተከትሎ የሚታዩና ለግብርናው ዘርፍ እጅግ አጋዥ የሆኑ ስራዎችን መሰራታቸውን አመላክተዋል።

ይህ የተፋሰስ ልማት ተግባር ከሚከናወኑ ጠቃሚ ስራዎች በተጓዳኝ ህብረተሰቡ እንደየ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ሰፊ እድል የፈጠረ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ በቀጣይም መላው አርሶአደሩ ይህንኑ አደረጃጀት በመጠቀም በበልግ ልማትና በሌሎችም ተግባራቶች ጠንካራ ስራ በመስራት እንደ ሀገር የመለወጥ ግብ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በተደራጀ መልኩ የተፈጥሮ ሀብታን በመጠበቅ ፡ በማልማትና በላቀ ደረጃ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ መግባባት በመፍጠር እንዲሁም ከሌላ ጊዜያቶች በተለየ መልኩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እንቅስቃሴ መደረጉን ተከትሎ ጠንካራ ስራ ተሰርቷል።

በአጠቃላይ በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ህዝቡ ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ በተለይም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችሉ በሌላ አካባቢዎች የምንሰማቸውና እንደ እዣ ወረዳ ቢከናወኑ ተብሎ የታለሙ እንደ ጠረጴዛማ እርከን እና በሌሎችም ስራዎች እጅግ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ ተሾመ ይህ ተሞክሮ በጠንካራ አደረጃጀቶች በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ተግባራዊ ማድረግ እንሚገባም አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በዘንድሮ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር 7ሺ 880 ለማልማት የታቀደ ሲሆን 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተመረጡ 28 ነባር ንዑስ ተፋሰሶችም የየተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ከታቀደው እቅድ በላይ ለማሳካት ተችሏል ብለዋል ።

በተፋሰስ ልማቱም በልዩ ትኩረት ከተፈፀሙ የፊዚካል ስትራክቸሮች መካከል የጠረጴዛ ርከን ፡ የአፈር ካብ ፡ ትሬንች ፡ የእንጨት ክትርና ሌሎችም ስራዎች በተመረጡ ቦታዎች መሰራታቸውን የገለፁት አቶ መቻል በቀጣይም ተግባሩ ከስነ -ህይወታዊ ስራ ጋር በማሳለጥ ቀጣይነት ያለውና አስተማሪ የሆነ ስራ ይሰራልም ብለዋል ።

ይህ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር እንደ ወረዳው መዝጊያ ፕሮግራም ቢደረግም እንኳ በቀጣይ በSLM ፕሮጀት የታቀፉ ቀበሌዎች እስከ ሰኔ ወር ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።

በፕሮግራሙ የተሳፈቱ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሰጡቱ አስተያየት በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ህዝቡ ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ ባለቤ ሆኖ ያለማንም ጠባቂነት ማከናወኑን የቻለበትና እጅግ የተለየና ለግብርና ምርታማነት ማሳደግ አስተዋፅኦ ያለው የጠረጴዛማ እርከን ስራ መከናወኑ ይበል የሚያሰኝና በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል።

በእለቱም በ2017ዓም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር ከSLM ፕሮጀክት ጋር በመቀናጀት የተከናወኑ የጠረጴዛማ እርከንና ሌሎችም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራቶች በተሳታፊዎች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በአፈፃፀም ግንባር ቀደም የሆኑ ቀበሌዎችና አደረጃጀቶች የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በዛሬው እለት

=====ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በዛሬው እለት

ከፌደራል ፓርላማ እና ከክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

👉 በብልጽግና ዘመን የምንከተለው መሰረታዊ እሳቤ የማይጠናቀቅ ፕሮጀክት አንጀምርም።

👉በክልሉ የተመረጡ አበይት የልማት አጀንዳዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመሩ እየተሰራ ነው።

👉 በክልሉ በእያንዳንዱ ወረዳ እና ቀበሌ ስንት የጤና፣የትምህርት ፣የውሃ፣የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሌሎችም ፣የተጠቃሚ ብዛት እና ሌሎች መረጃዎችን በቆጠራ የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል።

👉 በቂ መረጃ ከሌለ ስራ መምራት አይቻልም መረጃዎችን በርዕሰ መስተዳድር አማካሪዎች እና በፕላን እና ልማት ቢሮ አማካኝነት ጥናት ማካሔድ ተችሏል።

👉የጸጥታ፣የግብርና፣የገቢ፣የትምህርት፣የጤና፣የስራ እድል ፈጠራ፣ መሰረተ ልማት፣ንግድ እና ኢንቬስትመንት እንዲሁም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በየ እለቱ ክትትል የሚደረግባቸው አጀንዳዎች ናቸው።

👉 የክልሉ መንግስት ተመስርቶ ስራ ሲጀምር ከፍተኛ የእዳ ጫና ነበረበት ሆኖም ግን ጫናዎችን በመቋቋም መደበኛ ስራ ማስቀጠል ተችሏል።

👉 የ2016 በጀት ዓመት የምርት ዘመን የ3 ቢሊየን ብር ማዳበሪያ እንዲቀርብ ተደርጓል።

👉 ከአዳዲስ ይልቅ የነባር ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው።

👉 ሆኖም ግን በክልሉ በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክቶች በሚል እሳቤ 90 ፕሮጀክቶች በመቅረጽ ወደ ተግባር ተገብቷል። ከነዚህ ውስጥ 18 ያህሉ መድሀኒት ቤቶች ናቸው።

👉 የተጀመሩት ፕሮጀክቶች 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግባቸው ሲሆን ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ያደርጋሉ።

👉 በክልሉ 165 ኪ/ሜ የኮሪደር ልማት ስራ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

👉 ከመጋቢት 1/2017 ጀምሮ በ 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ በሰባት ከተሞች የቢሮ ግንባታ ይጀመራል።

👉 በክልሉ ባለፈው አመት ብቻ ከ5 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በህብረተሰብ ተሳትፎ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል።

👉 ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በተገቢው መንገድ ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነው።

👉የገቢ መሰረት ለማስፋት አዳዲስ አዋጆች አውጥተናል።

👉 በዚህ አመት ለ 350 ሺ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዷል።

👉 እስካሁን ባለው አፈጻጸም ለ215ሺ ዜጎች የስራ እድል ማሳካት ችለናል።

👉 በቡናና ቅመማ ቅመም ዘርፍ የኤክስፖርት አቅማችንን ለማሳደግ መስራት ይገባል።

ዘገባው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።

ለአገና ጤና ጣቢያ የአልትራሳውንድ የህክምና መሳሪያ ድጋፍ የተደረገ በመሆኑ በቅርብ ቀን አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተቋሙ አስታውቋል ።

========ለአገና ጤና ጣቢያ የአልትራሳውንድ የህክምና መሳሪያ ድጋፍ የተደረገ በመሆኑ በቅርብ ቀን አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተቋሙ አስታውቋል ።

ይህ በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል ድጋፍ የተደረገው የአልቶራሳውንዱ መሳሪያ እርጉዝ እናቶች ወደ ሌላ የህክምና ተቋም በመሄድ ይደርስባቸው የነበረው እንግልት የሚያስቀር ሲሆን የረጅም ጊዜ የተቋሙ ብሎም የማህበረሰቡ ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ተግባር መሆኑንም ተጠቁሟል።

የአገና ጤና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ከድር እንዳሉት ጤና ጣቢያው ገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከረጅም ጊዜ አንስቶ ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ሲያገለግል ቆይቷል ።

ጤና ጣቢያው ከሚሰጣቸው የህክምና አገልግሎት አንዱና ዋንኛው የእናቶችና ህፃናት ሞት ለመቀነስ የሚደረግ አገልግሎት ሲሆን በዚህም ረገድ እንደ ክልሉ ብሎም እንደ ሀገር ተሞክሮ የሚሆኑ ተግባራቶች እያከናወነ እንደሚገኝም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

በተለይም የእርጉዝ እናቶች ማረፊያ አገልግሎት በመጀመር እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ በጤና ተቋም እንዲገላገሉ በማድረጉ ረገድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ሸምሱ ለዚህም የሚያግዝ የእናቶች ማረፊያ ክፍል በመገንባት እናቶች እንደራሳቸው ቤት ምቾት እንዲሰማቸው ለማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በርካታ ተግባራት እየተሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል ።

በበጀት ዓመቱ በጤና ጣቢያው በእስካሁን ሂደት በርካታ እናቶች የቅድመ ወልዲ አገልግሎት በመስጠት ከታቀደው 108% ያህል መፈፀሙን የጠቆሙት ሀላፊው በግማሽ ዓመቱ ከታቀደው 105% እናቶች የወሊድ አገልግሎት ተሰጥቷልም ብለዋል ።

ይህ በክልሉ በክልሉ በኩል ድጋፍ የተደረገው የአልትራሳውንድ መሳሪያ ከዚህ በፊት ለጅም ጊዜ ጥያቄ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሸምሱ ይህም ከወሊድ ጋር ተያይዞ ትክክለኛ የፅንስ ሂደቶች በመከታተል ጤናማ እናትና ልጅ እንዲኖር ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ገልፀዋል ።

የአልትራሳውንድ አገልግሎቱ በከተማ መስተዳደሩና በወረዳው የሚገኙ 14 ቀበሌዎች ተጠቃሚ በማድረግ በዓመት ከ600 በላይ የሚሆኑ እናቶች አገልግሎት መስጠት የሚያችል መሆኑንም የገለፁት ሀላፊው እናቶች ለዚህ አገልግሎት ሲሉ ወደ ሌላ ተቋም በመሄድ ይደርስባቸው የነበረው እንግልት የሚያስቀር በመሆኑንም ይህን ድጋፍ ላደረገው የክልሉ ጤና ቢሮ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

በእናቶች ማረፊያ ክፍል አግኝተን ያነጋገርናቸው እናቶች በሰጡት አስተያየት በማረፊው ክፍላቸው ከህክምናው ክትትል በተጨማሪ ልክ ቤታቸው እንዳሉ አስፈላጊውን እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀው ከዚህ በተጨማሪ ሌላ ቦታ ሳይሄዱ በአቅራቢያቸው የአልትራሳውንድ ህክምና እንዲያገኙ ለደገፋቸው አካል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎ ወደውጭ የመላክ ዐቅም አሳድጋለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

=========ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎ ወደውጭ የመላክ ዐቅም አሳድጋለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

የካቲት 26፣ 2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካን በጎበኙበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ ሀገር ራስን የመቻል ጉዞዋን በማጠናከር ስሉጥ የሆነ የትውልድ ቅብብሎሽ ማረጋገጥ እንደሚገባት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ጥይቶችን የማምረት ሙከራዎች ብታደርግም፤ እስከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ድረስ ከውጭ በማስገባት ላይ ተመስርታ መቆየቷን አንስተዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎ ወደውጭ የመላክ አቅም አሳድጋለች ብለዋል ።

ይህ ርምጃ በምሉዕነት የተገነባ እና በሚገባ የታጠቀ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከማረጋገጥ አንፃር አበረታች ሥራ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከመከላከያ ግብዓቶች ባሻገር ሀገር የራሷን ምግብ ፣ መድኃኒት እና አልባሳት በበቂ ሁኔታ በማምረት እውነተኛ በራስ ምርት መተማመንን ማረጋገጥ እንደሚገባትም ነው አስገንዝበዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።