በክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በተሰጠው የተግባር ስልጠና በቂ እውቀትና ክህሎት ማግኘት መቻላቸውን ሰልጣኞ ተናገሩ

በክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በተሰጠው የተግባር ስልጠና በቂ እውቀትና ክህሎት ማግኘት መቻላቸውን ሰልጣኞ ተናገሩ

(ሆሳዕና፦ ጥቅምት 26/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለስምንት ተከታታይ ቀናት በወራቤ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።

በቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ እንደገለፁት ስልጠናው በየተቋማቱ አገልግሎት ላይ የሚዉለዉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ላይ ያተኮረ አድቫንስድ ኦፊስ ማሽን የተግባር ስልጠና እንደነበረ ተናግረዋል።

በየተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መታገዝ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ከበደ ለዚህም የዘርፉን የሰው ሀይልን በቴክኒካል ክህሎት ማስታጠቅና ማብቃት ተገቢ ነው ብለዋል።

ስልጠናው የአስልጣኞች ስልጠና እንደመሆኑ መጠን ለተቋማት የሚያስፈልጉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እንዳይበላሹ አስቀድሞ መከላከልና ሲባላሽም ለመጠገን የሚያስችል ስልጠና ነው ብለው

የአገልግሎት መሳሪያዎቹ ሲገዙ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን በእውቀት ላይ የተመሰረተ ግዢ ለመፈጸም የሚረዳ በመሆኑ ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደየመጡበት ተቋማት ላይ መተግበር ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ሰልጣኞቹም ከክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች፣ ከዞን እና ከልዩ ወረዳ የተወጣጡ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ከበደ ስልጠናው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሰልጣኞቹ እንደተናገሩት በተሰጠው የተግባር ስልጠና በቂ እውቀትና ክህሎት ማግኘት መቻላቸውን ገልፀው በየተቋማቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚፈጠረው ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።

በየተቋማቱ በቀላሉ ሊስተካከሉ የሚችሉ ነገር ግን በዘርፉ በቂ እውቀት ከላመኖሩ የተነሳ የሚጣሉ እና የሚባክነውን የመንግስት ንብረትን በቀላሉ ለማዳን ብሎም ወጪን ለመቆጠብ የሚያስችል ስልጠና ነው ብለው በቀጣይ ሌሎችን በማሰልጠን ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

የመደረኩ አሰልጣኝ የነበሩት ኢያሱ ጌታቸው እንደገለፁት ሰልጣኞቹ በቀጣይ በየተቋማቱ በትንሽ ብልሽት የቆሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በመጠገን አገልግሎት ላይ ለማዋል የሚረዳ እውቀት መቅሰማቸውን ገልፀው ድርጅቱ በሰልጣኞች እውቀት ሽግግር ላይ አበክሮ እየሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

አገር ልትገነባ የምትችለው በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን በመገንዘብ ወጣቱ ተገቢ ያልሆኑ የሚዲያ አጠቃቃሞችን በመታገል በሀገሪቱ ሰላምና እድገት ላይ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ ።

አገር ልትገነባ የምትችለው በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን በመገንዘብ ወጣቱ ተገቢ ያልሆኑ የሚዲያ አጠቃቃሞችን በመታገል በሀገሪቱ ሰላምና እድገት ላይ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ ።

ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም (አገና)

“ሚዲያ ለላቀ ልማት ለወረዳችን ከፍታና ለዘላቂ ሰላም የወጣቱ ሚና “በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከቀበሌ ለተወጣጡ ወጣቶች ስልጠና ተሰጥቷል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዘውዱ ዱላ በስልጠና መድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት የዚህ መድረክ ዋና አላማ በሀገር ሰላምና ግንባታ ላይ የወጣቱ ሚና ከፍ ማድረግ እንደሆነና እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ65%በላይ የወጣት ህበረተሰቡ ክፍል ሲሆን ይህም ወጣት አምራች ፡ ለቴክኖሎጂ ቅርብ ፡ ለሰላምና ኢኮኖሚ ግንባታ ዘብ የሚቆም ነው።

ሰላም ሚመጣው በዜጎች የተባበረ ተሳትፎ መሆኑን በመገንዘብ ሰላም ለማፅናት የተጀማመሩ ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ወጣቱ በባለቤትነት መሳተፍ ይገባዋል ያሉት አቶ ዘውዱ ወጣቱ የአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በመተንተን ክፍተቶችን ለይቶ በማገዝ ማህበረሰቡን ሊያማርሩ የሚችሉና የጥቂቶቹ ወይንም የግለሰብ ጉዳዮች ላልተፈለገ ቦታ ሊወስዱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ወጣቱ በማጤን የሰላም ዘብ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ ዛሬ ያለንባት ሀገር በብዙ መስዋዕትነት የቆየች ስትሆን በተለይም ቀደምት የነበሩ አባቶቻችን ብዙ ዋጋ ከፍለው ያቆያት እንደሆነና አሁን ያለው ትውልድ ለቀጣዩ ምን ሰርቶ ማለፍ እንዳለበት በመገንዘብ የድርሻችንን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ሌላኛው ዋንኛው የቀውስ ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ያለው ያልተገባ የሚዲያ አጠቃቀም ሀገራችን እንዳትረጋጋ እያደረጋት ካሉ ጉዳዮች አንዱና ዋንኛው መሆኑን በመገንዘብ ሚዲያ ለበጎ አላማና ለለውጥ መጠቀም ይገባልም ያሉት አቶ ተሾመ ለሀገር ብልጽግናና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የወጣቶች ተሳትፎ ከፍተኛ አበርክቶ ስላለው ወጣቱ በያለበት አካባቢ በሁሉም መስክ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ ነሪ በበኩላቸው ያለ ወጣቶች ሙሉ ተሳትፎ ሰላምንና ብልጽግናን በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደማይቻል በመገንዘብ ወጣቶች በሚዲያ አጠቃቀም ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች መሆን እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰዋል ።

በቀጣይም ወጣቶች በተሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች ሁሉ ውጤታማ በመሆን የሀገራቸውን ሰላምና ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል።

በእለቱም በወጣቱ ሚና እና በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤትና በወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት በኩል ሰነድ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የጉራጌ ብሄረሰብ ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲጎለብቱና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሰራው ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።

የጉራጌ ብሄረሰብ ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲጎለብቱና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሰራው ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።

ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም (አገና)

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ያሱራና ዋርቢያ ቀበሌ የሸራር ቤተሰብ ባካሄደው 12ኛ ዙር ንግስናና መሪ የመሾም ስነ ስርዓት ላይ ባርአዝማች ውቅያኖስ ተሰማ አንግሷል።

በፕሮግራሙ የታደሙት የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንዳሉት የጉራጌ ማህበረሰብ ዲሞክራሲን አስቀድሞ በመለማመድ የሚታወቅ ሲሆን ምንም ማያወላዳና ግልፅ የሆነ ከጥንት ጀምሮ ዘመናዊ የፍትህ ስርዓት ሳይኖር ተበዳይ ሳይገፋ አቅም የሌለው በጉልበተኞች እንዳይደፈጠጥ መብቱ እንዲከበር የራሱ ባህላዊ ስርዓት ያበጀ ነው።

አለም የእናቶች ቀን ብሎ ሀሳብ ሳይጀምረው የጉራጌ ማህበረሰብ የእናቶች በዓል አንትሮሸት፡ የልጃገረዶች ቀን ነቐ ፡ ይፍተዝፓር ፡ የሸት ሸረትና የመሳሰሉት ለእንስሳትም ጭምር ነፃነት የሚሰጥበት የመስቀልና አረፋ በዓል ላይ በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ባህሎችን ያስቀመጠ ነው ያሉት ሀላፊዋ ዛሬም በእዣ ወረዳ ያሱራና ዋርቢያ ቀበሌ በሸራር ቤተሰብ ያየነው የንግስናና መሪ የመምረጥ ስርዓት የሰለጠነው አለም እንኳ ብዙ የሚጋፋበትና በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ከማድረግ ይልቅ አላስፈላጊ ነውጥ ውስጥ ሚገባበትን ጉዳይ እንዴት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ስልጣንን ከአንዱ ወደ አንዱ እጅግ በሚደንቅ መንገድ ማሸጋገር እንደሚቻል ያስተማረ ነው ብለዋል ።

ፕሮግራሙም ሌሎችም ጎሳዎችና ሀይማኖቶች ሳይነጣጥል በአንድነት መንፈስ መደረጉ እጅግ የሚደንቅ በመሆኑ ይህንን እንደ ባህል ተጠብቆ እንዲኖር የመመዝገብ ስራ ለመስራት ጥረት ይደረጋልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው በሀገራችን ኢትዮጵያ በባለፉት ሰባት ዓመታት የጉራጌ ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲጎለብቱና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ መንግስት ጥረት አድርጓል።

ጉራጌ ከራሱ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ ድንቅ ባህልና መተዳደሪያ ደንቦች ያለው ፡ አምራች፡ ሌላውን በፍቅር አቅፎና ተባብሮ የሚኖር ማህበረሰብ እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው ተናግረዋል።

በዛሬው እለትም የተካሄደው ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየውን በእዣ ወረዳ ከሚጠቀሱ ጎሳዎች አንዱ የሆነውን የሸራር ቤተሰብ ከ800 ዓመት በፊት ጀምሮ የነበረው አዝማችነት ሴራ በያስሁራ ቀበሌ የባር አዝማች ተሰማ ፊጣ ስልጣን በልጅ ልጃቸውን ለ12ኛ ዙር የማስተላለፍ ስርዓት መደረጉን ማህበረሰባችን በስልጡን መንገድ ስልጣንን የማስተላለፍ ባህል ማሳያ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ ስልጣኑ የተረከቡት ባርአዝማች ውቅያኖስ ተሰማ በአግባቡ ህዝቡን በመምራት ሀላፊነቱ መወጣት እንዳለበትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የዚህ ዝግጅት አስተባባሪ አቶ ደንድር ባባድር በበኩላቸው ዛሬ የተደረገው የወርቅ አንባር የዛሬ 800 ዓመት ጀምሮ ሲተላለፍ የመጣ ታሪካዊ ቅርስ ሲሆኑ አንባሮቹም ሁለት የወርቅና አንድ የብር በድምሩ 3 መሆናቸው ጠቅሰዋል ።

ታሪካዊ አመጣጡም በዚህ ጎሳ ቤተሰብ ከንጉስ ዋረብየ ጀምሮ ብሽንየንበር እያለ በዛሬው እለት የነገሱት ባርአዝማች ውቅያኖስ ተሰማ ድረስ የመጣ ባህላዊ ስርዓት ነው ብለዋል።

በዛሬው እለት ሀላፊነት የተሰጣቸው የዚህ ቤተሰብ አንድነት ጠብቆ የማስኬድ ፡ እንደ እዣ ብሎም እንደ ጉራጌ በሚደረጉ ውይይቶችና ልማቶች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት ይገባቸዋልም ብለዋል።

ንግስናና መሪ የመሾም ስነ – ስርዓት በተለያዩ ባህላዊ ስነ ስርዓቶች የተካሄደ ሲሆን ለአዲሱ ንጉስም የብርና የቁሳቁስ ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ።

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ።

ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት

20ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ”ዴሞክራዊ መግባባት ለህብረ ብሄረዊ አንድነት” በሚል ቃል በነገው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአት የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ ያሳተፈ ማህበር አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይካሄዳል።

በዚህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁሉም የወረዳችን ህብረተሰብ ተሳታፊ እንዲሆን የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጥሪውን ያስተላልፍል። መረጃው ከፅ/ቤቱ ድህረ ገፅ አገኘን!!