በዛሬው ዕለት በእዣ ወረዳ ህ/ሥ/ጽ/ቤት አዘጋጅነት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

በዛሬው ዕለት በእዣ ወረዳ ህ/ሥ/ጽ/ቤት አዘጋጅነት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

በስልጠናውም የእዣ ወረዳ ህብረት ስራ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌትነት ወልዴ ጨምሮ የቀበሌ አደራጅ ባለሙያዎች ገንዘብ ያዦች የሂሳብ ሰራተኞች የመጋዘን ሀላፊዮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ልዩልዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተውበታል ።

በቆይታውም የማህበራት ማደራጀትና ምዝገባ የሠራተኞች የሥራ ሥነ-ምግባር የሂሳብ አያያዝ እና አሰራር ስርዓት የአፈር ማዳበርያ አቅርቦት እና ስርጭት ላይ ሰፊ ግንዛቤ እደሚፈጠር ይጠበቃል።

ዝርዝር ይኖረናል ይጠብቁን

“በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ወደ ዓላማ ተኮር ህዝብ ግንኙነት ” በሚል መሪ ቃል ሚዲያኖ ኮሚኒኬሽን ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

“በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ወደ ዓላማ ተኮር ህዝብ ግንኙነት ” በሚል መሪ ቃል ሚዲያኖ ኮሚኒኬሽን ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

ህዳር 2/2018 ዓም

በስልጠናው ሚዲያ ያለው አቅም በደንብ በመረዳት ለበጎ አላማ መጠቀምና የሚዲያ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤን በማዳበር እንደ ሀገር የተጀምረው የብልፅግና ጉዞ ዘርፉ ያለው ፋይዳ የላቀ በመሆኑ በትኩረት መስራት ይገባል ።

በመድረኩም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ ፡ የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ጨምሮ ሌሎችም የወረዳው አመራሮች ተሳታፊ ናቸው ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የስነህዝብ ምክርቤትና ቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋም የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።

ከወረዳው የህዝብ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የዜጎችን የማልማት አቅም በማሳደግ የምግብ ዋስትናን እንዲረጋገጥ ለስነ-ህዝብ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

ህዳር 1/2018 ዓም

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የስነህዝብ ምክርቤትና ቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋም የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።

የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ በመድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት መንግስት የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና ፈጣንና ዘላቂ ልማት ዕውን ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

የሰው ሀይል ልማት ላይ መስራት እና ያለዉን የህዝብ ቁጥር ካለን የኢኮኖሚ አቅም ጋር እንዲመጣጠን ማድረግ ይገባል ያሉት ም/አስተዳዳሪው የማህበረሰቡ ፍላጎት ካለው የኢኮኖሚ አቅም ጋር መመጣጠን ካልቻለ ለስራ አጥነት ቁጥር መጨመር እና ሌሎችም ተያያዥ ማህበራዊ ቀውሶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ በመረዳት ለዚህ ዘርፍ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ።

በመሆኑም በዛሬው እለት የተቋቋሙትን የስነ ህዝብ ምክር ቤት ኮሜቴ ተግባርና ሀላፊነታቸው በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደመቀ ሀብቴ በበኩላቸው ስነ ህዝብ በባህሪው ዘርፉ ብዙ እንደመሆኑ መጠን ስነህዝብ በአንድ መ/ቤት ወይም ተቋም የተናጥል እርምጃ ብቻ የሚፈታ ጉዳይ ሳይሆን የተለያዩ ሴ/ር መ/ቤቶችና ድርጅቶችን የተባበረና የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ አብይ የልማት አጀንዳ ነው፡፡

በመሆኑም በወረዳው የስነ ህዝብ ስራዎችን በበላይነት የሚያስተባብርና የሚመራ የስነ ህዝብ ምከር ቤትና ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ተውጣቶ በስነ ህዝብ ጉዳይ የሜንስትሪሚንግ ተግባር ሲያከናውንና ቴክኒካዊ ድጋፍ ሲሰጥ የነበረን የቴክኒክ ኮሚቴ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲቻል ይህ የስነ ህዝብ ምከር ቤትና የቴክኒክ ኮሚቴ ማቋቋሚያ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም አመላክተዋል።

በቀጣይም እነዚህ አካላት የተቀናጀ አሰራር በመፍጠር የስነህዝብ ጉዳይ ከልማት ዕቅድ ጋር በማሳለጥ ዘላቂ ልማትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በባለቤትነትመንፈስ ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል ።

ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየትም ከወረዳው የህዝብ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የዜጎችን የማልማት አቅም በማሳደግ የምግብ ዋስትናን እንዲረጋገጥ ለስነ-ህዝብ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልፀው ለዚህም ዛሬ የተቋቋሙትን የስነህዝብ ምክር ቤት ኮሚቴዎች በተናበበና በተቀናጀ መንገድ መስራት ይገባቸዋልም ብለዋል።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደረገ ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደረገ ።

ህዳር 2ቀን 2018 ዓ.ም

በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት የማስ ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴ ባሻገር ለአብሮነት እና ወንድማማችነት ያለው ድርሻ የጎላ በመሆኑ ስፖርቱን ማደበር የሚገባ ሲሆን ተነቃቅሶ ስፖርትን መስራት በማህበረሰቡ ዘንድ ሊለመድ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዳበር ጤናን ከማስጠበቅ አኳያ በቀን ውስጥ ለምናደርገው የስራ እንቅስቃሴ ንቁ እንድንሆን የሚያደርግ በመሆኑ ሊዳብር የሚገባ ሲሆን ዛሬ 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተካሄደው ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሌሎችም ጊዜያቶች ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ ነሪ በበኩላቸው ማስ ስፖርት ጤንነታችን ለመጠበቅ እና የእርስ በርስን ትውውቅን ለማዳበር ያለው አስተዋዕጾ የላቀ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ፕሮግራም በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአትጀምሮ የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ ያሳተፈ ማህበር አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተዳካሂዷል።