



=======ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለበጎ አላማ በመጠቀም የሀገር ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ “ወደ ዓላማ ተኮር ህዝብ ግንኙነት ” በሚል መሪ ቃል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተጥቷል።
በመድረኩም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት ሚዲያን ለበጎ አላማ በማዋል እንደ ወረዳው ብሎም እንደ ሀገር እየተሰሩ የሚገኙ የሰላምና የልማት ተግባራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ ፣ ባለሙያውና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸወን መወጣት ይገባቸዋል።
ሚዲያ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጠናከር ለህዝብ ተጠቃሚነት የሚሰራ መሆን ይጠበቅበታል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በዚህ ረገድ ከአመራሩ ጀምሮ ያሉትን ውስንነቶችን በመቅረፍ በዘርፉ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን የብልፅግናን ጉዞ እውን እንዲሆን መስራት ይገባልም ብለዋል ።
የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ተግባራት አለማቀፋዊ ግንኙነቶችን የሚፈጥሩ በመሆናቸው በዘርፉ የሚሳተፉ አካላት የወረዳው ብሎም የሀገሪቱ መልካም ገፅታ በማሳወቅ ረገድ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል።
እውነትን ማእከል ያደረገ ትርክት መፍጠር ፡ ሀሰተኛ መረጃዎች ማጋለጥ ፡ ትክክለኛውን መረጃ ማስተላለፍና ማጋራት ይገባል ያሉት አቶ ተሾመ በዚህ ረገድም አመራሩ በቁርጠኝነት መሳተፍ ይገባልም ብለዋል።
በእለቱም የእዣ ወረዳ እረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብዱራህማን ሀሰን የስልጠና ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ተቋሙም የመንግስት ስራዎች በማሳወቅ የህዝብና የመንግስት አቅም በማቀናጀት እና በማገናኘት ልማትን መሰረት ያደረገ ስራ ለማከናወን በትኩረት መስራት እንደሚገባም ተመላክቷል።
በእቱም የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፡ የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን እንዲሁም የእዣ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፔጆች ተከታዮቻቸውን ለማሳደግ የሚዲያ ቻሌንጅ ተከናውኗል።




