የእዣ ወረዳ ም/ቤት 2018 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ አመት 4ኛ ዙር 13ዓመት 42ኛ መደበኛ የምክክር መድረክ /ፎረም/ በቆጠር ገድራ ቀበሌ አስተናጋጅነት ተካሂደ ።

====ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ እና በሞዴልነት እየተመረጡ የመጡት የወረዳ እና የቀበሌ ም/ቤቶች ይበል የሚያሰኙ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል እዳለባቸው ተገለፀ ።

ቀን 04/03/2018

የእዣ ወረዳ ም/ቤት 2018 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ አመት 4ኛ ዙር 13ዓመት 42ኛ መደበኛ የምክክር መድረክ /ፎረም/ በቆጠር ገድራ ቀበሌ አስተናጋጅነት ተካሂደ ።

የወረዳው አፈ ጉባዔ አቶ ሙከረም በደዊ እንደገለፁት ወረዳችን በዞኑ ጥሩ አፈፃፀም ካላቸው ም/ቤቶች አንዱ እደመሆኑ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣበት ሂደት እዳለ ጠቅሰው አሁንም ወጥ በሆነ መንገድ በተገቢው ሁኔታ መቀጠል እዳለበት ጠቅሰው የክትትል እና ቁጥጥር ተግባር በማጠናከር የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ከአሰራር ስረዓት እና ከህገ-መንግስት አንፃር ችግሮቹ መቀረፍ እዳለባቸው ገልፀው

በመድረኩም የቀበሌ ም/ቤቶች 1ኛ ሩብ ዓመት የድጋፍ ሪፖርት የ2018 የፎርም ዕቅድ የ2018 አነስተኛ መመዘኛዎች የ2018 የምዘና ነጥብ የአለፈውን ዙር ቃለ ጉባዔ እና ቀጣይ መደረግ ያለባቸው አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት አፈ-ጉባዔው በሙሉ ድምፅ ያፀደቁ ሲሆን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በመቀናጀት እና ያሉብንን ጉለትዎች በመድፈን ማህበረሰባችንን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ሀላፊነታችንን በሚገባ መወጣት እደሚገባ ጠይቀዋል

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው ህዝብ የሚያነሳውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄና ማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን ልንፈታ የተሰጠንን ትልቅ ሃላፊነትን በሚገባ በመረዳት ለህዝባችን ሁለተናዊ ተጠቃሚነት መሠራት እደሚገባ ገልፀው ህዝቡ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት ከማድረግ አንፃር ስራዎች የአሰራር አደረጃጀት መመርያ ተአትሎ በጥንቃቄ በመግባባት በቅንጅት እና በግልፀኝነት ሊሰሩ እደሚገባ ገልፀዋል

የእዣ ወረዳ ም/ቤት የህግ ማውጣት ክትትል ቁጥጥር ስራ ሂደት አስተባባሬ አቶ ተስፋዬ ካሳ የሁሉንም ቀበሌዎች ም/ቤት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በአጠቃላይ የቀበሌ ም/ቤቱ ያለውን ጥንካሬ እና ተግዳሮቶቹን የተሰሩ ጠንካራ ስራዎች ሳያዘናጉን ትኩረታችንን ጉለቶችን ለመሙላት ስተቶችን የማረም እና ስራችንን ውጤታማ ማረግ ላይ ሊተኮር እደሚገባ ገልፀው

የቀበሌ ም/ቤቶች የጋራ ቅንጅታዊ ተግባር አንፃር ከወረዳ አመራር ጀምሮ እስከ ቀበሌ አመራር ድረስ የተሄደበት እረቀት እደለ እና ከሴቶች ተሳትፎ አንፃር ያሉጉለቶችን እና ሌሎች ተግዳሮቶችን በማረም ማህበረሰባችንን በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚ ማድረግ እደሚገባ ገልፀዋል።

በጉባኤውም የእዣ ወረዳ ዋና አፈ ጉባኤ ሙከረም በደዊ የእዣ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሶመ ስራኒ የወረዳው ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አየለች ሀይሌ እንዲሁም የወረዳው ልዩ ልዩ አመራሮች የእዣ ወረዳ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች የም/ቤት ማኔጅመንቶች እና ባለሙያዎች የቀበሌ አፈ-ጉባዔዎች ሊቀመንበርዎች ስራ አስኪያጆች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ከተሳታፊ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በመጨረሻም አጀዳዎቹ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ እና የወረዳ ተቋማት በየ ዘርፋቸው ውጤታማ የነበሩ የወረዳው ተቋማትን የቀበሌ ም/ቤቶችን እንዲሁም ባለሙያዎችን የዋንጫ የገንዘብ እና የእውቅና ሰርተፍኬት በመሸለም ተጠናቋል ። ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነው ።

በዞኑ በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች በዘላቂነት ለማስቀጠል አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅበታል

በዞኑ በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች በዘላቂነት ለማስቀጠል አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅበታል፦የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ

ህዳር 4/2018ዓ.ም (አገና)

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ወቅታዊ የንቅናቄ ተግባራት አፈፃፀም የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በግምገማው ወቅት እንዳሉት በዞኑ በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች፣ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልፀው፣ በዘላቂነት ለማስቀጠል አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

ግብርና የድህነታችን መውጫ፣ የኢኮኖሚያችን ማረጋገጫ በመሆኑ በአሁን ሰዓት ያሉን የመስኖ አቅም በአግባቡ በመጠቀም ግብርናውን ማዘመንና የምግብ ዋስትናችንን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ አስታውቀዋል።

አቶ ላጫ አክለውም የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት ኢኒሼቲቮች የህብረተሰቡ መሰረታዊ ጥያቄ የሚፈቱ እንደመሆናቸው መጠን የኮሪደር ልማት ስራ የህብረተሰቡ የስራ ባህልን የቀየረ በመሆኑ የተጀማመሩ አመርቂ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል።

በተለይ የከተማ የኮሪደር ስራ ቤቶቹ ከፈረሱ በኋላ ጊዜ ሳይሰጣቸው በአፋጣኝ ሰርቶ መጨረስ እንደሚገባና የዞናችን ከተሞች ደግሞ የጉራጌ ማህበረሰብ የሚመጥኑ መሆን አለባቸው ብለዋል።

ጀፎረን ከገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ጋር በማስተሳሰር ጀፎረን ይዘቱን ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚገባ መክረዋል።

በቀጣይ ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ፣ ነባር የገበያ ማእከላት ወደ ዘመናዊ ገበያ ማእከልነት መቀየርና የወባን በሽታ በንቅናቄ በመምራት ወረርሽኙ በአፋጣኝ መከላከል እንደሚገባ አቶ ላጫ መመሪያ ሰጥተዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል በንቅናቄ እንዲሰሩ የወረዱ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ገልጸው በቀጣይ በዞናችን ያሉ የመልማት አቅሞችን በአግባቡ በመጠቀም ከዚም የበለጠ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

እነዚህ ስራዎች በውጤታማነት ለማከናወን አመራሩ በቁርጠኝነት ፣በታማኝነት፣ በኃላፊነት መስራትና ትግሉን ይበልጥ እንዲያጠናከር አስገንዝበዋል።

ስራዎች በጥራት ፣በፍጥነት ፣በስፋት እንዲሁም በፍትሀዊነትና በግልጸኝነት በመስራት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት።

አቶ አለማየሁ አክለውም አመራሩ ነባራዊ ሁኔታን ማጥናት፣የህግ የበላይነት ማረጋገጥና የተሰጠው ተግባር በጥንቃቄ ሰርቶ ማስረከብ እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎች እንደተናገሩት ከድህነት ለመሻገር ግብርናው ላይ በትኩረት እየሰሩ እንደሆነ ገልጸው በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል፣በመስኖ ልማት ስራዎችና በሰብል አሰባሰብ ላይ በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በከተማና በገጠር የሚሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ህብረተሰቡ ያሳተፉ የውይይትና የሀብት አሰባሰብ ተግባራቶች እየተከናወኑ ሲሆን እነዚህም ለከተሞች ውበትን፣ የህብረሰቡን ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መመለሻ ቁልፍ ተግባር መሆኑ የገለፁት ሀሳብ ሰጪዎቹ ደረሰኝ የመቀበል ልምዳችን በማጎልበት የገቢ አቅማችን ማሳደግ ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት ተግባር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገለጸው በቀጣይም በሁሉም ዘርፎች የተጀማመሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አጠናክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ