






=====አመራሩ የወሰደውን ስልጠና እንደ ተጨማሪና አዳጊ እድል በመጠቀም በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራት ህብረተሰቡን የሚመጥን ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅበት የጉራጌ ዞን ዋና አስተደዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጹ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ማዕከል “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ”በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር ለከፍተኛና መካከለኛ አመራር ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን በማስመልከት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ለሰልጣኞች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተደዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደተናገሩት ለቱሪዝም ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ዘርፉ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።በመሆኑም ጉራጌ ያለው የቱሪዝም እምቅ አቅም ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ተረድቶ መስራት ከሁሉም ይጠበቃል።
የአመጋገብ ስርዓት፣ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት፣የዳኝነት ስርአት፣ገዳማትና መስጂዶች፣ጥብቅ ደኖች፣ድንቅ የአኗኗር ዘይቤ ያለው ማህበረሰብ ሲሆን ነቁወ፣መስቀል፣አረፋ፣ አንትሮሽት፣ሳምር፣ ጀፎረ፣ባህላዊ ቁሳቁሶችና የሌሎችም እሴት ባለቤት መሆኑን ለአብነት አንስተው እነዚህን በአግባቡ በመጠቀም ዞኑ የቱሪዝም ማእከል ማድረግ ያስፈልጋል።
የገጠር ትራንስፎርሜሽን በሁሉም ዘርፍ ብልጽግናውን የተረጋገጠ ማህበረሰብ መፍጠር ስለመሆኑን ያስገነዘቡት አቶ ላጫ በተለይ ግብርናን ከኢኮኖሚ ጋር በማስተሳሰር ለስራ እድል ፈጠራና ለምግብ ዋስትና ማረጋገጫ እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል።
በዚህ ዘርፍ በዞኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በአግባቡ በመስራት በጠረጴዛማ እርከን የተሰሩ ስራዎች ከምርታማነት ባሻገር የአካባቢው ስነ ምህዳሩን በመጠበቅ ውበትን እንዲጎናጸፍ አድርጎታል ነው ያሉት።
ማህበረሰቡ ለከተሞች እድገት ያለው አመለካከት እጅግ የተሻሻለ በመሆኑ የጉራጌ ዞን ከተሞች ማህበረሰቡ የሚገልጹ መሆን እንዳለባቸው መክረው የኮሪደር ልማት ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።
አቶ ላጫ አክለውም በከተሞች ኢንቨስትመንት መሳብ፣ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣በፕላን መመራት፣መሬትን በአግባቡ መጠቀም፣ውብና ጽዱ ማድረግና የከተማ ግብርናን አጠናክሮ በመስራት ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ተናግረዋል።
የሀገር ኢኮኖሚ ለማሳደግ ፈጠራና ኢንድስትሪው ማስተሳሰር ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው የስራ ባህላችን ማሻሻልና ለኢንድስትሪ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠት እንሚገባ አመላክቷል።
ለዚህም ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ አካባቢዎች በመለየት ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ ማሳደግ ይቻላል።
እንደ አቶ ላጫ ገለጻ በዞኑ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚፈጅ ወጪ የካፒታል ፕሮጀክት ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በመንገድ፣በንጹህ መጠጥ ውሃ፣በጤና፣በግብርና ፣ በትምህርትና በሌሎችም አመርቂ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በመሆኑም አመራሩ በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራት ህብረተሰቡን የሚመጥን ስራ በማከናወን ይጠበቅበታል።
ጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን












