







======የመጌቻ መስኖ ፕሮጀክት ወደ ተግባር እንዲገባ በተከናወነው ስራ ከ 12 ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች እየለማ መሆኑን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ውሃ ፡ ማዕድንና ኤነርጂ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ።
ጥር 16/2018 ዓም
የእዣ ወረዳ ውሃ ፡ ማዕድንና ኤነርጂ ልማት ፅ/ቤቶ ሀላፊ አቶ ተሻለ ከፋ እንደገለፁት እንደ መንግስት ድህነት ለመቅረፍ ግብርናው የማይተካ ሚና እንዳለው በመገንዘብ በዘርፉም በትኩረት የተሰራባቸው ያለው የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፡ ምርትና ምርታማነት ማሳደግና ተረጂነትን ለማስቀረት አንድም መሬት ፆሙ ማደር የለበት በሚል ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ።
የግብርናው ዘርፍ ለማሳደግ ደግሞ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ስራ ማጠናከር ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ዋንኛው መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው እንደ ወረዳው በ2018 ዓም መስኖ ልማት ፕሮጀክት ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መመደብ ጀምሮ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ተጨባጭ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል ።
አሁን በስፋት መስኖ እየለማበት ያለው የመጌቻ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ከዓምና ጀምሮ የወረዳው መንግስት በጀት በመመደብና ከ2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 300 ሜትር የካናል ጥገና በማድረግ በአሁን ሰዓት ከ 12 ሄክታር በላይ መሬት በድንች ፡ በሽንኩረት ዘር ብዜት እንዲሁም በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች እየለማበት ይገኛልም ብለዋል ።
በዚህ ፕሮጀክት ለዘመናት ሳይታረሱ የነበሩ መሬቶች እና ባህርዛፍ አንስቶ በማረስ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛልም ያሉት አቶ ተሻለ የመጌቻ መስኖ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ እስከ 250 ሄክታር ማልማት የሚያስችል እና እስከ ዝግባቦቶ ቀበሌ ድረስ የሚያስጠቅም በመሆኑ እንደ ወረዳው በመስኖ ልማት የነበሩ ውስንነት ለመቅረፍ የሚያስችልም እንደሆነ አስአድተዋል ።
እንደ ወረዳው ከዚህ ከመጌቻ መስኖ ባለፈ በአንድ ሚሊየን ብር ገደማ ኔሸ ቀበሌ እየተጠናቀቀ ያለ አዲስ የወንዝ ጠለፋ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ስራ አለ ያሉት አቶ ተሻለ ከዚህ ባሻገር በ2014 ተጀምሮ ለብዙ ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን ግዙፉ የይነሸሆ የመስኖ ግንባታ በአጭር ጊዜ ሚጠናቀቅበት ውል ተገብቶ ስራዎች የተጀመሩ ሲሆን ይህ ደግሙ ይህንኑ ዘርፍ የሚያሳድግና በርካታ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እጅግ ተስፋ የሚሰጥ ነውም ብለዋል ።
በቀጣይ ይህንን እና ሌሎችም ፕሮጀክቶች አካባቢ ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት በዘርፉ የሚጠበቀው ግብ በላቀ ደረጃ እንዲፈፀም በቅንጅት እንደሚሰራም የገለፁት አቶ ተሻለ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተግባር ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ እንዲከናወኑ ከወረዳው እስከ ፌዴራል መንግስት ለተሰጠው ትኩረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በአጓይተረህ ቀበሌ በመገቻ መስኖ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሆኑ አርሶአደሮችም ቦታው ለዘመናት ያልታረሰና በባህር ዛፍ የተወረረም ጭምር እንደነበረር አስታውሰው አሁን የወረዳው መንግስት የመስኖ ፕሮጀኮቱ በአግባቡ እንዲጠገን አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረጉ የተለያ ሰብሎች በማልማት እየተጠቀሙ እና ሌሎችም ከእነሱ ብዙ ልምድ እየወሰደ መሆኑንም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።





