(ሆሳዕና ጥር 19/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፓርቲና የመንግስት ተግባራት የ6 ወራት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው

ባለፉት 6 ወራት የተመዘገቡ ውጤቶች ማስቀጠል እና ያጋጠሙ ጉድለቶችን ፈጥኖ በማረም ለላቀ ስኬት መትጋት ይገባል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

(ሆሳዕና ጥር 19/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፓርቲና የመንግስት ተግባራት የ6 ወራት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) እንደገለጹት በክልሉ ባለፉት 6 ወራት በፓርቲ እና በመንግስት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ ተግባቦት መፍጠር የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በየደረጃው የተገመገሙ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ መለየት የሚያስችል መድረክ መሆኑን አብራርተዋል።

ባለፉት በ6 ወራት የተመዘገቡ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ጉድለቶችን መለየት የሚያስችል መድረክ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በአፈጻጸም ረገድ የተስተዋሉ መልካም ልምዶችን ማስቀጠል እና ውስንነቶችን ደግሞ ፈጥኖ ማረም ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

በክልሉ በተቀመጠው አቅጣጫ እና እቅድ፣ስራው በቅንጅት የተመራበት ሂደት ይፈተሻል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

አመራሩ ተቀናጅቶ ለአንድ አላማ መትጋት አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሁሉንም ተግባራት በጊዜ የለንም መንፈስ በውጤታማነት ማከናወን ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

የአስተሳሰብ ቀረጻ፣ ያለንበት ደረጃ ፣ያልተሻገርናቸው ፈተናዎች፣የመፍጠር፣የመፍጠን እና የዝላይ ስትራቴጂ በመከተል ስራን ማከናወን አብይ ጉዳይ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሀዊ፣ዲሞክራሲያዊ እና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን አመራሩ ሚናውን መወጣት እንዳለበት የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

በተስፋዬ መኮንን

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአራት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ዉይይት አደረገ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአራት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ዉይይት አደረገ።

ጥር 21/2018 ዓ.ም (አገና)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በአራት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ዝርዝር ዉይይት በማድረግ አዋጆቹን ለክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

መስተደድር ምክር ቤቱ ዛሬ ማምሻዉን በበይነ መረብ አማካይነት ባካሄደው ስብሰባ የተወያየባቸዉ ረቂቅ አዋጆች፦

1/ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 10/2016 (ማሻሻያ) ረቂቅ አዋጅ፣

2/ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣

3/ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጫት ኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣

4/ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት የወጣ ረቂቅ አዋጅ የሚሉት መሆናቸዉ ተመልክቷል።

መረጃው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።