የ2018 ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት እወጃ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በተገኙበት በእዣ ወረዳ ሻመነ ቀበሌ የካር ንዑስ ተፋሰስ እየተካሄደ ይገኛል።

====የ2018 ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት እወጃ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በተገኙበት በእዣ ወረዳ ሻመነ ቀበሌ የካር ንዑስ ተፋሰስ እየተካሄደ ይገኛል።

ጥር 26/2018(ወልቂጤ)

በዘንድሮ ዓመት በጉራጌ ዞን 88 ሺ 581 ሄክታር መሬት በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት እንደሚለማ ተገልጿል።

በዚህም በ270 ኑዑስ ተፋሰሶች የሚሰራ ሲሆን ከ4 መቶ ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከዚህ በፊት በዞኑ በተሰሩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የግብርና ምርትና ምርታማነትን እንዲጨምር አድርጓል።

የተፋሰስ ስራ ባህርዛፍ ከማንሳት፣ያልታረሱ መሬቶችን ከማረስ ጋር አስተሳስሮ በመስራት የግብርና ምርታማነት ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።

በእዣ ወረዳ በ28 ኑኡስ ተፋሰሶች 9ሺ 850 ሄክታር መሬት በተፋሰስ ይለማል ነው የተባለው።

በፕሮግራሙ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን፣የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ፣የዞኑ የስራ ኃላፊዎች፣የወረዳው አመራሮችና አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መንገድ ትኩረት ሰጥቶ እያበረታታ እና ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለፀ።

መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መንገድ ትኩረት ሰጥቶ እያበረታታ እና ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ቀን 26/05/2018

በእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበር ጉዳዮች ጽ/ቤት ከወረደው መንግስት ጋር በመቀናጀት 300,000 ብር ወጪ በማድረግ ለዘጠኝ (9) የአካል ጉዳተኞች ዌልቸርና እንዲሁም ለሌሎች ለአራት (4) አካል ጉዳተኞች የክራንች ድጋፍ አደረገ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እዳሉት አካል ጉዳተኞችን ማገዝ ከኢትዮጵያዊነት ባህል አኳያና ከመንፈሳዊ ርካታ በተጨማሪ ለሃገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ትልቅ አስተዋፆ እዳለው በመረዳት መንግስት እና ፖርቲ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና።

በተለይም እንደ ሃገር አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር እና ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀው ።

በተቻለ መጠን ሁሉም አካል ጉዳተኞችን ማቀፍ መደገፍ ምቹ ነገሮችን መፍጠር ተገቢ እንደሆነና በየትኛውም በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አካል ጉዳተኞችን ማበረታታት እንደሚገባ እና በተለያዩ ጊዜም ይህ በጎ ተግባር ሊቀጥል እና ሊጎለብት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ የሰ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትግስት መንግስቴ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት እስከ 300,000 ሺ ብር ወጪ በማድረግ ለ9 አካል ጉዳተኞች ና ለተጨማሪ 4 አካል ጉዳተኞች የክራንች ድጋፍ ያደረገ መሆኑን ገልጸው።

በወረዳው ማዕከል ለተለያዩ አካል ጉዳተኞች ሲንቀሳቀሱ መጸዳጃ እንዳይቸገሩ በማሰብ የአካል ጉዳተኞች ምቹ የሚሆን ሽንት ቤት መግባቱን ገልጸው ከዚህም በተጨማሪ ሌሎችም ድጋፊችን እየተደረገላቸው እንደሆነ አስረድተው።

አሁንም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከመቼውም ጊዜ በላይ ከዘመኑ እሳቤ ጋር አብሮ የሚራመድ የሰለጠነ አስተሳሰብ እና ዘላቂ ለውጥ በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ማህበረሰብን ለማሳወቅ እና የተሻለ ማህበራዊ እድገት ለማስመዝገብ እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ለመርዳት ሁሉም አካላት የበኩሉን ሊወጣ እደሚገባ አስገንዝበዋል።

አካል ጉዳተኞችን በበኩላቸው የወረደው መንግስት በተለያየ ጊዜ አካል ጉዳተኞች እየረዳና እያገዘ እንደሆነ ገልፀው አሁንም ከመንግስት ባገኙት ድጋፍ መደሳቸውንና በተለያየ ጊዜም ይህ ተግባር ሊቀጥል እንደሚገባና የተደረገላቸውን የድጋፍ እቃዎች በመረከብ የድጋፍ ስርዓቱ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።