ብልፅግና የጠንካራ ፓርቲ እና መንግስት ተምሳሌት በመሆኑ ምርጫው በፓርቲው አሸናፊነት በማጠናቀቅ ኢትዮጵያ በከፍታ ማማ ላይ እንድትሆን አባላቱ የድርሻው መወጣት እንዳለበት ተገለፀ።
የካቲት 24/2018 ዓ.ም (አገና)
የእዣ ወረዳ እና የአገና ከተማ አስተዳደር በጋራ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በኬሮድ አዳራሽ ተካሂዷል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት እንደሚታወቀው ባለፉት የለውጥ አመታት ብልፅግና ፓርቲና የመደመር መንግስት የሃገር የቁልቁለት የእድገት ጉዞ በመቀየር ወደ ከፍታ ማማ እንድትወጣ ከቅጅና ምርኮ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ስርዓት ለማላቀቅ እንዲሁም የነበሩ ስብራቶች ለማከም በርካታ ተግባራቶች ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል ።
በተለይም ነፃ ፡ ገለልተኛ ብቃት ያላቸው ተቋማት እንዲገነቡ ትክክለኛ የሪፎርም ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን በሂደትም ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለም ዋና አስተዳዳሪው አመላክተዋል።
ጠንካራ ፓርቲ እና መንግስት የሚመሰርተው በምርጫ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ በመሆኑም የ7ኛ ዙር ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ ሁለት መንታ ግቦች ያሉት ሲሆን አንደኛው ምርጫው ነፃ ፡ ፍትሃዊ ፡ ዲሞክራሲያዊ ፡ ገለልተኛና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን መስራት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ምርጫው በፓርቲያችን አሸናፊነት አጠናቀን ጠንካራ ፓርቲና መንግስት መገንባት አለብንም ብለዋል።
በመሆኑም ህዝባችን ያልተፈቱ የልማትም ይሁን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚፈታለት የብልፅግና ፓርቲ መሆኑን አምኖ በቀጣይ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር ለመቀየር የሚሰራው ፓርቲ ድምፁን እንዲሰጥ ከወዲሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የእዣ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ የባለፉት ሰባት ዓመታት ለዘመናት የተወዘፉና የተተበተቡ ፈተናዎች የገጠሟት ቢሆንም ይህንን በመቀልበስ አለም ሊማርባቸው የሚችሉና የተማረባቸው ዘርፈ ብዙ ውጤቶች አስመዝግባለች ።
ብልፅግና በአንድ ዘርፍ ታስሮ የነበረው የሀገራችን እድገት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ አቅጣጫ በመከተል በቱሪዝም ፡ ከከተማ እስከ ገጠር ኮሪደር ፡ ከፕሪቶሪያ እስከ ቱርክ አንካራ ፡ ከሶማሊያ እስከ አረብኤምሬት የፀና የዲፕሎማሲ ስራ ፡ ከጥላቻ ወደ ትብብር ፡ ከብተና ወደ መደመር ያመጣ ታላቅና ባለራዕይ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ብልፅግና የዘንድሮ ምርጫ የሚያካሄደው በተግባር ተፈትኖ አዳጊ የሆኑ ውጤቶች አስመዝግቦ እንጂ እንደሌሎች በማይዳሰስና በማይጨበጥ ተስፋ እንዳልሆነም አቶ ተሾመ ጨምረው ገልፀዋል።
የ2018 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ በወረዳችንና በከተማችን ስናካሄድ ሀገራችን ብሎም ጉራጌ ዞንን የምንክስበት ከመሆኑም ባሻገር ከ2013 ዓ.ም የምርጫ ጉለታችን በመማር ከአሉባልታና ከከፋፋይ አጀንዳዎች ተላቀን የፓርቲያችን ብቁና አሻጋሪነት በውል ተገንዝበን ሁላችንም ለምርጫው ስኬታማነት መረባረብ ይገባናል ያሉት ሀላፊው የስንዴ ነዶ በመምረጥና በማስመረጥ በብልፅግና አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ ሀላፊነታችን እንወጣም ብለዋል።
በእለቱም የአገና ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ክልል ክብሩ የ2018 የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ሰነድ አቅርበዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ግጥሞችና መዝሙሮች የቀረቡ ሲሆን ለቀበሌ ሊቀመናብርቶች የብልፅግና ፓርቲ ምልክት በሆነው የስንዴ ነዶ ምልክት ተበርክቶላቸዋል ሲል የቀገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።