ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር”

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የካቲት 26/2018 ዓም

የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ሲሆን ምልክቱ የመደመር ፡ አንድነት እና ትብብር መገለጫዎችን የያዘ መሆኑም ተመላክቷል ።

በተለዩ ቀበሌዎች ተዛዙረው የተመለከቱት የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም አወል እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ ህብረ ብሄራዊ አንድነት በመከተል ሃገርን መምራት ከጀመረ ወዲህ በፓሊቲካዊ ፡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶች ማስመዘገብ መቻሉን ገልጸዋል።

ምርጫ ለአንድ ሀገር የዲሞክራሲ መገለጫና ህዝቡ የሚወክለውንና የሚመራውን ፓርቲ በድምፁ የሚወስንበትና የሚያረጋግጥበት መሆኑን ገልፀው ማህበረሳባችንም በሀገራችን ሁሉአቀፍ እድገትና ብልፅግና እያስመዘገበ ያለውን ፓርቲ ብልፅግናን እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ እና ክልል አቀፍ ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት የሚጣልበትና የሕዝብ ሉዓላዊነት በተግባር የሚረጋገጥበት ነው ያሉት ረዳት የመንግስት ተጠሪው የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት የሆነው “የስንዴ ነዶ” የመደመር ፡ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ መሆኑን አብራርተዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን በማሸጋገር ተምሳሌት ሀገር ለማድረግ በግልጽ ራዕይ በዕውቀት እና ተጨባጭ ተግባራዊ ውጤታማነት የታጀበ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉንም ጨምረው የገለፁት አቶ ኢብራሂም እንደ ወረዳው በሁሉም ቀበሌ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፡ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሀዊ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ምርጫ በማድረግ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል የተቀመጠውን ራዕይ ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ተሳታፊ አካላትም የብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ጥቂት አመታት መንግስት በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካው መስክ ባስመዘገባቸው ውጤቶች መጠቀማቸውን ጠቅሰው የፓርቲያቸውን የምርጫ ምልክትነት የስንዴ ነዶ በመምረጥ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ በመሆን ከቀድሞው ስህተታችን በመማር ፓርቲውን በመምረጥ ለመካስ ተዘጋጅተናልም ብለዋል።