በከተሞች የተከናወኑ ስራዎችን ይበልጥ በጥራት እና በመጠን በማስፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

በከተሞች የተከናወኑ ስራዎችን ይበልጥ በጥራት እና በመጠን በማስፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

መጋቢት 3/2018 ዓም

የእዣ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 8ወር እቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ገምግሟል።

በእለቱም የእዣ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው አየለ እንዳሉት ከተሞች ውብ ፡ ምቹና ለነዋሪዎች ፅዱና ሳቢ እንዲሆኑ ማህበረሰቡ ባለቤት በማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ።

በከተሞች የተከናወኑ ተግባራት ስራዎችን ይበልጥ በጥራት እና በመጠን በማስፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በማዘጋጃ ከተሞችና በጥንስስ ከተሞች በማህበረሰብ ተሳትፎና በመንግስት ካፒታል በጀት የከተማ ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ችግር የነበሩ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል ከተሞች ለነዋሪዎች ተስማሚና ምቹ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በእለቱም በፅ/ቤቱ ምክትልና የማስፈፀም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኑራዲስ ነስሩ እንዲሁም የፅ/ቤቱ ም/ሀላፊና የመሬት ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አንዳምላክ እንዳላ በኩል የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

እንደ ወረዳው በ2018 በጀት ዓም በእስካሁን ሂደት ለተደራጁ ማህበራት መሬት 1.1192 ሄክታር መዘጋጀቱ ፡ ለአገልግሎት ተቋማት የሚውል መሬት 1.8786 ሄ/ር የተዘጋጀ ሲሆን ለንግድ ኢንቨስትመንት የሚውል መሬት 2.4926ሄ/ር ለማዘጋጀት መቻሉንም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ቤት ለሚገነቡ ማህበራት 1.13ሄ/ር መሬት ለማስተላለፍ የተቻለ ሲሆን ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚውል 1.895ሄ/ር መተላለፉንምን ፡ 96 ለአዲስና ነባር የይዞታ ማረጋገጫ መሰጠተን ፡ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለመሰረተ-ልማት ግንባታዎች ሀብት ማሰባሰብ 2,449,900 መከናወኑንም በሪፖርቱ ተገልፆአል ።

አዲስ ጠጠር መንገድ ግንባታ 6.6 ኪ.ሜ የተከናወነ ሲሆን አዲስ መንገድ ከፈታና ጠረጋ 8 ኪ/ሜ መከናወኑንና ሌሎችም አበረታች ሥራዎችን መሰራታቸው ተብራርቷል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በማዘጋጃ ከተሞች በባለፉት 8 ወራት በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ አበረታች ተግባራት በማጠናከር ውስንነቶችን ከማዘጋጃ የውስጥ ገቢ ከሊዝ ውዝፍ፣ አመታዊ ክፍያ ፣የመሰረተ ልማት ስራዎች ቁጥጥር የነዋሪ አደረጃጀት ለማረም በቀጣይ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።