




በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ345 በላይ ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና መሰጠት ተጀመረ
መጋቢት 28/2018 (አገና)
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለሚገኙ ለ3መቶ 45 መምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና መስጠት መጀመሩን የእዣ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት አስታወቀ።
የእዣ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ በአገና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የምዘና ሂደቱን በይፋ አስጀምረዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ በሙያ ብቃት ምዘናና ፈተና 230 ወንድ 115 ሴት በድምሩ 345 የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ይመዘናሉ ብለዋል።
ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ የፈተና ማዕከላትን የማደራጀት፣ ተፈታኞችንና ፈተና አስፈጻሚዎችን የመለየት ስራ ቀድሞ ሲከናወን ቆይቷል ያሉት ሀላፊው ይህ ምዘና መምህራን በሙያቸው ያላቸውን ክብር ከመጨመሩ ባለፈ፣ በራስ የመተማመን አቅማቸውን የሚያሳድግና ከጥቅማ ጥቅማቸው ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ ተመላክቷል።



