የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ዲጂታል ሥርዓት ሥራ አስጀመረ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ዲጂታል ሥርዓት ሥራ አስጀመረ

********************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ነዋሪዎች የሕዝብ አገልግሎቶችን ባሉበት ቦታ ሆነው ማግኘት የሚያስችላቸውን አዲስ የበይነ መረብ (ኦንላይን) አገልግሎት ሥርዓት በይፋ ሥራ አስጀምሯል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ አዲሱ ሥርዓት የራስን ችግር በራስ አቅም እና በቴክኖሎጂ ለመቅረፍ እየተሠሩ ላሉ ሀገራዊ ሥራዎች በተግባራዊ ማሳያነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ዘመናዊ አሠራር ነዋሪዎች አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋሙ በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው፣ ባሉበት ቦታ ሆነው ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ ከማድረጉም ባሻገር፣ የራሳቸውን መረጃ በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉበትን ዕድል የሚፈጥር ነው።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሤ በበኩላቸው፣ ቴክኖሎጂው ዜጎች ቀልጣፋ እና ከብልሹ አሠራር የጸዳ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም፣ ሥርዓቱ በተለይም የሐሰተኛ ሰነዶች ዝውውርን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል።

በተጨማሪም ነዋሪዎች አገልግሎቱን በሚያገኙበት ጊዜ በግል መረጃዎቻቸው ላይ ስህተት ቢፈጠር፣ ካሉበት ቦታ ሆነው በራሳቸው ማስተካከል እንዲችሉ ሥርዓቱ ይፈቅዳል።

ይህም የተገልጋዮችን እንግልት በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ በተሻለ ምቾት አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል።

ደንበኞች ወደ Portal.aacrrsa.gov.et ድረ-ገጽ በመግባት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፣ እነዚህ እና መሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንደ ሀገር የተያዘውን “ዲጂታል ኢትዮጵያ” ራዕይ እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተጠቁሟል።

በብሩክታዊት ተገኝ

“ሳይንስ ይመራናል ቴክኖሎጂ ያስቀድመናል”

በጉራጌ ዞን ለ5ኛ ጊዜ በተካሄደው የሳይስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የፈጠራ ስራ ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ መዋቅሮችና ተወዳዳሪዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጠ!!

ሰኔ 02/2018 ዓ.ም(ወልቂጤ)

“ሳይንስ ይመራናል ቴክኖሎጂ ያስቀድመናል” በሚል መሪ ቃል የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ከዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያና ከሌሎች ባለድርሻ አካካት ጋር በቅንጅት የተዘጋጀው የዞኑ 5ተኛው ዙር የሳይንስና ቴክኖጂ እንደዚሁም የፈጠራ ስራ ውድድ ተጠናቋል።

በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ የወጡ መዋቅሮች፣ተቋማትና የፈጠራ ባለቤቶች የዋንጫ፣ የሜዳሊያ የገንዘብና የእውቅና ሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዚህ መሰረት በአጠቃላይ ከመዋቅሮች በሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ዉድድር

1ኛ.ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር

2ኛ እዣ ወረዳ አስተዳደር

3ኛ እኖር ወረዳ በመሆን ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የዋንጫና የእውቅና ሰርተፊኬት አግኝቶዋል ።

በተመሳሳይ መልኩ በክፍል ደረጃቸው ተለይተው ከ7ኛ እና 8ኛ ፣ ከ9ኛ እና 10ኛ ፣ከ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ለተወዳደሩ ተማሪዎች፣የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ፣ የግል ተወዳዳሪዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ የሜዳለያ ገንዘብና የእውቅና ሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቷል።

በተጨማሪም በፈጠራ ስራ ተሳታፊ ለሆኑ መዋቅሮችና ለፕሮግራሙ መሳካት ድጋፍና ትብብር ላደረጉ ተቋማት የእውቅና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

የስነ-ምግባር ችግር ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አልፎ ለአደጋ መንስኤ መሆን እንደሌለባቸው ተገለፀ ።

የስነ-ምግባር ችግር ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አልፎ ለአደጋ መንስኤ መሆን እንደሌለባቸው ተገለፀ ።

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም (አገና)

በእዣ ወረዳ እና አገና ከተማ መስተዳድር ለሚገኙ ባለ ሁለት ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር አሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት እና የስነ ባህሪ ተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷል።

መድረኩ የመሩት የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ግሩም ወ/ሰንበት የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ እያስከተለው ያለው ህይወት መቅጠፍና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ለመቀነስ አሽከርካሪዎች ያላቸው ከፍተኛ ሀላፊነት ተገንዝበው ዘወትር በጥንቃቄ ማሽከርከር እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

አክለውም መንገድ ትራፊክ አደጋ እንደ ሀገር እያስከተለው ያለው የሰው ልጅ ህይወት መቅጠፍ ፡ ከፍተኛ የንብረት መውደምና አልፎም ተርፎም ቤተሰብ እስከመበተን ያለው ቀውስ ለመቀነስ ስነ-ምግባር ተላብሶና ህግን ጠንቅቆ በማወቅ ማሽከርከር እንደሚገባም ለሰልጣኞቹ አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ መልስ በበኩላቸው የትራንስፖርት አገልግልግሎት በአጠቃላይ የሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እድገት ላይ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚይዝ ገለፀው አሽከርካሪዎች የሚሸከሙት የሰው ነብሰ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ እንቅሰቃሴዎች በስነምግባር እና በጥንቃቄ የተሞላ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል ።

ሃላፊው አክለውም የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ እያስከተለው ያለው ህይወት ማሳጣትና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ለመቀነስ አሽከርካሪዎች አሁን የተሰጣቸው ስልጠና በተግባር በማዋል በጥንቃቄ ማሽከርከር እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የአገና ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሞገስ ንማኒ በኩላቸው የመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ ከከተማው ብሎም ከወረዳው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ስነ-ባህርይና ስነ-ምግባር አኳያ ስንመለከት አንዳንድ ጠንቃቃ እና ትሁት አሽከርካሪዎች እንዳሉ ሁሉ በተለይ በአንዳንድ የባለ 3እግር ባጃጅና አነስተኛ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የስነ-ምግባር ችግር ምክንያት በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አልፎ ለአደጋ መንስኤ ሲሆኑ ይታያልም ብለዋል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዳይሮክትሬት የትምህርት ስልጠና ግንዛቤ ማስጨበጫ ኤክስፐርት አቶ ክፍሌ አሼቦ የስልጠናው ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት በአሽከርካሪዎች ከሚስተዋሉ የጥንቃቄ ችግሮችና ለመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ ከሆኑት መካከል ለአብነት ያለብቃት ማሽከርከር ፡ የተሽከርካሪ ደህንነት ሳያረጋግጡ ማሽከርከር ፡ ከተፈቀደ የፍጥነት ወሰን ማለፍ ፡ የመንገድ ትራፊክ ህጎች አለማክበር በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል ።

በስልጠናው ተሳታፊ አሽከርካሪዎችም ስልጠናው እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊ በመሆኑ በሚያሽከረክሩበት ወቅትም የበለጠ እንዲጠነቀቁ የሚያደርግ እንደሆነም በአስተያየታቸው ተናግረዋል በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች ለተቸገሩ ወገኖቻች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ስልጠናው ተጠናቋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው ።