የፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ፍጥነታቸውን ይበልጥ ማሻሻል እንደሚገባ ተገለፀ።
ሰኔ 24/2018 ዓም
የእዣ ወረዳ የፍትህ ማሻሻያ አብይ ኮሚቴ ባለፉት ወራት በወረዳው ፍትህ ተቋማት የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።
የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት በወረዳ የፍትህ ተቋማት ተቀናጅተው በመስራት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ይበልጥ ማረጋገጥ ይገባል ።
የፍትህ ተቋማት አገግሎታቸው ከሰብአዊ መብት መከበርና መጠበቅ ጋር ማቆራኘት ይገባቸዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በጥራትና በብቃት አጣርቶ ወንጀለኞችን ለህግ በማቅረብ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ከሌብነትና ብልሹ አሰራሮች ነፃ በመሆን የፍት ፡ ፖሊስና ፍርድ ቤቶች በመቀናጀት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅዶች ለማሳካት በትኩረት በመስራት ህብረተሰቡ በፍትህ ተቋማት ላይ ተገቢውን እምነት እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባም አቶ ዘውዱ ጨምረው ተናግረዋል።
በቀጣይም በዘርፉ ውጤታማ ስራ በመስራት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው በግምገማ መድረኩ ተመላክቷል።