





የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ለተለያዩ ኢኮኖሚያውና ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ እና አካል ጉዳተኞች ድጋፍ አደረገ ።
ሀምሌ 20/2018 ዓም
በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ለተለያዩ ኢኮኖሚያውና ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ እና አካል ጉዳተኞች ለእርቢ የሚሆኑ ፍየልና በግ ድጋፍ አደረገ ።
የፅ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት መንግስቱ ድጋፍ በተደረገበት ወቅት እንዳሉት እንደ ወረዳው ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችና አካል ጉዳተኞች በመለየትና ፅ/ቤቱ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር መጠነ ሰፊ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።
አንድ ሰው “ሰው” ነው ከሚያሰኙት በርካታ ባህርያቶች አንዱ ከጎኑ ያለ ወገኑ መርዳት ሲችል ነው ያሉት ወ/ሮ ትግስት ሁሉም አካል በዚህ ቅዱስ ሀሳብ በመሳተፍ በእንዲህ መሰል ተግባር ተሳታፊ ሊሆን ይገባል ብለዋል ።
ዛሬ የተደረገውም ድጋፍ ከወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ከተሰበሰበው የ1% ድጋፍ መሆኑን ያመላከቱት ወ/ሮ ትግስት በዚህ ድጋፍ ከወረዳው ከሚገኙ ቀበሌዎች ለከፋ ችግር የተጋለጡ 17 የሚሆኑ ወገኖች እና አካል ጉዳተኞች በመለየት ለእያንዳንዳቸው ለእርቢ የሚሆኑ አንድ በግ ወይንም ፍየል ድጋፍ መደረጉንም ገልፀዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸውንም ወገኖችም በሰጡት አስተያየትም በተደረገላቸው ድጋፍ እንደተደሰቱና በቀጣይም እራሳቸው እንዲችሉ የሚያነሳሳ በመሆኑ ድጋፍ ላደረገላቸዎም አካል ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
See less



