“ጤና ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከምርታማነት፣ ከትምህርትና ከማህበረሰቡ አጠቃላይ ዕድገት ጋር የተቆራኘ ነው” አቶ ዘውዱ ዱላ የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ!!

“ጤና ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከምርታማነት፣ ከትምህርትና ከማህበረሰቡ አጠቃላይ ዕድገት ጋር የተቆራኘ ነው” አቶ ዘውዱ ዱላ የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ!!

መስከረም 26/2019 ዓም

የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የጤና ጉባኤ አካሂዷል።

“ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የእዣ ወረዳ ጤና ጉባኤ ተካሄደ።

ጉባኤው በ2018 በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም፣ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበሩ የጤና አጀንዳዎችንና የሥራ አቅጣጫዎችን ለመወሰን ያለመ ነው።

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ ጤና ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከምርታማነት፣ ከትምህርትና ከማህበረሰቡ አጠቃላይ ዕድገት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ገልጸዋል።

የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት የሚመልሱ አዳዲስ አጀንዳዎችን በመንደፍና በተግባር በማስረገጥ ጤናማና ምርታማ ማህበረሰብ ለመገንባት በጋራ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የጤና ሥራዎች ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲቀጥሉ ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመው፤ በየደረጃው ያለ አመራር የህዝብን አጀንዳ መሠረት በማድረግ ጤናን እንደ ቁልፍ የማህበረሰብ አጀንዳ በመቁጠር መሥራት እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በተለይም የግልና የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ፣ መንደሮችን ጽዱና ለኑሮ ምቹ ማድረግ የጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ ዋና አካል በመሆኑ ሁሉም አካል በኃላፊነት ሊሳተፍ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በመቀጠል የእዣ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሰዒድ የ2018 በጀት ዓመት የጤና ዘርፉን አፈጻጸም፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ የታዩ ክፍተቶችንና ለ2019 በጀት ዓመት የተያዙ የሥራ አቅጣጫዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

አቶ መሀመድ በንግግራቸው በ2018 በጤና ዘርፉ የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን ማስቀጠልና ያሉ ክፍተቶችን በጋራ መፍታት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በተጨማሪም የጤና አገልግሎቱ በሁሉም ደረጃ ተደራሽ፣ ጥራት ያለውና ለማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን የጤና ባለሙያዎች፣ አመራሮችና ማህበረሰቡ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ከጤና ጽህፈት ቤቱ የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 የሥራ አቅጣጫ አቀራረብ በኋላ በቀረቡት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፣ በማህበረሰብ ተሳትፎ፣ በጤና ተቋማት አፈጻጸምና በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶች ላይ ሀሳቦችን አንስተዋል።

በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችና የቀረቡ ጥያቄዎች በመጠናቀቅ፣ የጤና ዘርፉን ውጤታማነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትብብር መሥራትና የተለዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ሥራ ላይ በተገቢው መንገድ ማስተካከል እንደሚገባ በመግባባት ላይ ተደርሷል።

የጉባኤው ማጠቃለያ አካል በመሆንም በ2018 በጀት ዓመት በጤና ዘርፍ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩና ለጤና ሥራዎች አስፈላጊ ድጋፍና አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት የማበረታቻና የዕውቅና ሽልማት ተበርክቷል።

ዕውቅናው ለሞዴል እናቶች፣ ለጤና ባለሙያዎች፣ ለጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች፣ ለተቋማት፣ ለሊቀመንበሮች እንዲሁም በጤናው ዘርፍ በጎ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ድርጅቶችና ሌሎች አካላት የተሰጠ ሲሆን፣ ሽልማቱ በዘርፉ የተመዘገቡ ጥሩ ተሞክሮዎችን ለማበረታታትና በቀጣይም የበለጠ ውጤት እንዲመዘገብ ለማነሳሳት ያለመ ነው።

See less

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ የሥራ ርክክብ አደረጉ

=======አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ የሥራ ርክክብ አደረጉ

ወራቤ ፣መስከረም 26/2019 ፣ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን

የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሆነው አዲስ የተሾሙት አቶ ደምስ ገብሬ ከቀድሞ የቢሮው ኃላፊ ከነበሩት ከአቶ ሰላሙ አማዶ ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

እስካሁን በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችና በቀጣይ የለውጥ ዓመታት የሚተገበሩ የልማት ዕቅዶችን ለአዲሱ ኃላፊ የማስተዋወቅና የማስረከብ ሥራ ተከናወኗል።

በርክክቡ ወቅት የቀድሞው የቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰላሙ አማዶ ለአዲሱ ኃላፊ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚከናወኑ የሥራ እንቅስቃሴዎች ገለጻ አድርጓል።

አቶ ሰላሙ አማዶ በቆይታቸው ከተቋሙ ማኔጅመንትና አጠቃላይ ሠራተኞች በመቀናጀት ያከናወኗቸውን የሥራ ስኬቶች የገለጹ ሲሆን

አዲስ ለተሾሙት የቢሮው ኃላፊ መልካም የስራ ዘመንና የትጋት ጊዜ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የቢሮው ለአዲሱ ኃላፊ አቀባበል እና ለቀድሞው ኃላፊ ሽኝት ያደረገ ሲሆን የቢሮው ምክትል ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት በሰጡት አስተያየት የቀድሞ ኃላፊ ላበረከቱት አገልግሎትና ላከናወኑት የሥራ አፈጻጸም አድናቆታቸውን ገልጸው፣ በቀጣይ የሥራ ዘመን መልካም ስኬትን ተመኝተዋል።

አዲሱ የቢሮ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበው፤ በሚኖራቸው ቆይታ ቢሮውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በሥራ ርክክቡ ወቅት የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች፣ የማኔጅመንት አባላትና እንዲሁም ጠቅላላ ሠራተኞች ተገኝተዋል።

See less