ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!”

ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!” — አቶ ሙከረም በደዊ

ቀን 02/2019 ዓ.ም

​19ኛው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በእዣ ወረዳ በተለያዩ ዝግጅቶችና በቃል መሐላ ስነ-ስርዓት በድምቀት ተከበረ።

​በዕለቱ የእዣ ወረዳ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሙከረም በደዊ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰንደቅ ዓላማችን የነጻነታችን፣ የአርበኝነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የማንነታችን ግርማ በመሆኑ ለአንድነታችንና ለብሔራዊ መግባባታችን መጠናከር የጎላ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

​በስነ-ስርዓቱ ከተላለፉት ዋና ዋና መልዕክቶችና ከተገባው ቃል መሐላ :- የአንድነትና የነጻነት ምልክት፦ ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት፣ ለአንድነታችን፣ ለነጻነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዘላቂ መቆሚያ ነው።

​ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፦ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን አስወግደን፣ ሀገራችንን በልማትና በዴሞክራሲ ጎዳና የሕዝቦችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን።

​የጋራ ትግልና ቁርጠኝነት፦ ያጋጠሙ ችግሮችን በአንድነትና በጋራ ስሜት በማስወገድ፣ በዓመቱ የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችን ለማሳካት በሰንደቅ ዓላማችን ፊት ቃል እንገባለን።

See less

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን በዛሬው ዕለት ሰጥቷል። በዚህም መሠረት:-

=========የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን በዛሬው ዕለት ሰጥቷል። በዚህም መሠረት:-

1ኛ) ኢንጂነር አተረፈ ታምራት… የኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር

2ኛ) ኢንጂነር ሲቲ ሙስጠፋ .. . ም/ዋና ዳይሬክተርና የመንግስት ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ግንባታ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

3ኛ) ኢንጂነር ምህረተአብ ሳሙኤል .. . ም/ዋና ዳይሬክተርና የመንግስት ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ዲዛይንና ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

4ኛ) ወ/ሮ ትብለጥ ኢስጢፋኖስ .. . ም/ዋና ዳይሬክተርና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማትና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

ለሁሉም ተሿሚዎች አመራሮቻችን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

See less

#ትልቅሀገር#ትልቅሕዝብ#ታላቅርዕይ

=====የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

ሠንደቅ ዓላማችን የመደመር ዕሴታችን፣ የአንድነታችንና የኢትዮጵያ ከፍታ ምልክታችን ነው!

ዛሬ 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አክብረናል!

ሠንደቅ ዓላማ የቀደምት አባቶቻችንን የመሥዋዕትነት ታሪክ የሚያስታውሰን፣ የዛሬ ትጋታችንን የሚያንፀባርቅና የነገውን የብልፅግና ራዕያችንን የሚያመላክት የሀገራችን የከፍታ ዓርማ ነው።

የመደመር መንግሥት ዋነኛ ትኩረት ኢትዮጵያን በአንድነት፣ በሰላም፣ በልማትና በሁለንተናዊ ብልጽግና ወደ ላቀ ከፍታ ማሸጋገር ነው።

ሠንደቅ ዓላማችን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ እንጂ የልዩነታችን ምንጭ መሆን የለበትም። በብሔር፣ በቋንቋ፣ በባህልና በእምነት የተለያየን ብንሆንም፣ በኢትዮጵያዊነታችንና በጋራ የልማት ራዕያችን አንድ ነን።

የመደመር ዕሳቤም ልዩነቶቻችንን እንደ ሀብት በመቁጠር፣ የጋራ ዕሴቶቻችንን በማጠናከርና በትብብር የሀገራችንን ታላቅነት በተግባር ለማረጋገጥ ያነሳሳናል።

በዚህ ታላቅ ብሔራዊ ቀን፣ ሠንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገን እያውለበለብን ለአንድነታችን፣ ለሰላማችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለሀገራችን ብልጽግና ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር እናረጋግጥ።

እንኳን 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሰን!

#ትልቅሀገር#ትልቅሕዝብ#ታላቅርዕይ

See less

የጉራጊኛ ቋንቋ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን — አዲስ የምስራች

ወሄም ሳረናሁም፣ሳረንደም

የጉራጊኛ ቋንቋ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን — አዲስ የምስራች!

**^^

Ministry of Innovation and Technology በ STRIDE Ethiopia 2 Summit 2026 ላይ አዘጋጅቶ ይፋ ባደረገው አዲስ Digital Literacy Content Platform ላይ የዲጂታል እውቀት ማበልጸጊያ ይዘቶቹ (Contents) ከተዘጋጁባቸው 10 ቋንቋዎች ጉራጊኛ አንዱ ሆኗል!

ይህ ስኬት ጉራጊኛን የትምህርት፣ የሥራ እና የቴክኖሎጂ ቋንቋ ለማድረግ ሲደረግ የነበረው ጥረት ፍሬ ማፍራቱን ያሳያል።

በጉራጊኛ የተዘጋጁትን ይዘቶች በሚከተለው ሊንክ በመግባት ይጎብኙ፡ 🔗https://www.dlc.gov.et/public/index.php/search?categoryId=0&langId=8&search=

ይዘቶቹን ተመልክተው ያለዎትን አስተያየት እና ግብረ-መልስ ኮመንት ላይ ያጋሩን!

#DigitalLiteracy#Guragigna#WolkiteUniversity#TechnologyInLocalLanguages#DigitalEthiopia See less

See less

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያ ከዞኑ አስተባባሪ አካላት ጋር በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

======የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያ ከዞኑ አስተባባሪ አካላት ጋር በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

ጥቅምት 01/2019(ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን አስተባባሪ አባላት በቀጣይ በዞኑ በሚፈፀሙ የፖለቲካ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል ።

በዞኑ ሰላምን የማፅናትና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ተመላክቷል።

ባለፉት አመታት የተጀመሩ ህዝቡን ያሳተፉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በህዝባዊ ውይይት መድረኮች ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ታቅዶ ይሰራል ተብሏል።

የብልፅግና ፓርቲ በህዝብ ውስጥ ያሉትን ፀጋዎች ለይቶ በማውጣት፣በማቀድና ህዝብን ባሳተፈ መልኩ በመስራት ብልፅግናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራና ይህንኑ በዞኑ እውን ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።

በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ ዞኑ የሚታወቅባቸው ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሆነና ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችም በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲውሉ ይደረጋል ተብሏል።

በቀይ በታቀዱ ተግባራት የዞኑ ህዝብና ተወላጆች እንደዚሁም አጋር አካላት ከዞኑ አመራር ጎን በመቆም ሊያግዙ እንደሚገባም ተጠይቋል።

See less

ምክር ቤቱ አቶ ክብሩ ፈቀደ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አድርጎ ሰየመ።

=====ምክር ቤቱ አቶ ክብሩ ፈቀደ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አድርጎ ሰየመ።

ጥቅም 1/2019 (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 14ተኛ ዓመት 12ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው አቶ ክብሩ ፈቀደ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ ሆነው እንዲያገለግሉ ሰይሟል።

See less

ምክር ቤቱ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ብዛ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሰየመ።

=====ምክር ቤቱ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ብዛ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሰየመ።

ጥቅም 1/2019 (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 14ተኛ ዓመት 12ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው አቶ መብራቴ ወልደማሪያም ብዛ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው እንዲያገለግሉ ሰይሟል።

See less