በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

የልማትና የመልካም አስተዳር ችግሮችን በመቅረፍ የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት መረጋገጥ እንዲችል የባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ ስለመሆኑ ተገለፀ

‎ጥቅምት 24/2019 ዓም

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

በመድረኩም የተገኙት የእዣ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰለሞን ዘርጋ በመድረኩም ተገኝተው እንዳሉት ተቋሙ የመንግስት አሰራርና መመሪያዎች በተገቢው ተግባራዊ መሆን እንዲችሉ በማስቻል ተቋማት ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

በተቋማትና በቀበሌ ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥ ስነ- ምግባር የታከለበት አገልጋይ ለህዝብ መስጠት እንደሚገባ ጨምረው የገለፁት አቶ ሰለሞን ሁሉም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡን ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት ቀልጣፋ አገልግሎት፣ ለህዝቡ ለመስጠት የህዝብ ክንፎችና የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይ ሁሉም የሚመለከታቸው ባልድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናክር እንደሚገባም አመላክተዋል።

የእዣ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ ወይኑ አቅንዳ በበኩላቸው በወረዳው በሚገኙ በመንግስት ተቋምና በቀበሌ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ባለሙያው በአገልጋይነት መንፈስ ሊሰራ ይገባል።

በበጀት አመቱ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡን ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት እንዲሆን ተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ የሚያስችል ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተው ተቋማት በአገልግሎትአሰጣጥ ላይ የሚገጥማቸውን ችግር ሊፈታ በሚያስችል መልኩ ሁለንተናዊ ድጋፍ የማድረግ ፣ የለውጥ ስራዎችን ፣ አደረጃጀትና አሰራሮችን የማጠናከ ስራ በትኩረት የሚሰሩ መሆኑን ተናግዋል ።

በመድረኩ የ2019 ዓ.ም በ1ኛ ሩብ አመት በሴክተሩ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በተቋሙ የልማት እቅድ ባለሙያ በዝርዝር ቀርቦ ከባለድርሻ አካላት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮች ምላሽና አስተያየቶች ተሰጥቶባቸዋል።