
==================================
ጋበር የእዣው ነፃ ኣውጪ
*****
የእዣን ህብረተሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ነሐሴ 17ቀን 2014ዓም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን
ተመዝግቦ የተመሰረተው ጋበር የበጎ አድራጎት ማህበር ቅደሜ ህዳር 01ቀን 2016ዓም በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች ለብርቱ
ጉዳይ ቀጠሮ ይዟል።
‘የጉራጌን ማህበረሰብ ማህበራዊ መሰረቶች መሸርሸር ፤ኣሳሣቢነቱና የመውጫው መንገድ’’ የሚል ፅሁፍ በሁሉም ቀበሌ ከሚገኙ
ከሁሉም እድሜና ፆታ የተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይትና ምክክር ያደርጋል።በዚሁ ጉዳይ ላይ ሠፊ ውይይት እና ምክክር ተደርጎና
ከህብረተሰቡ የቀረቡትን የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመጨበጥ ጋበር ከወረዳችን የመንግስት አመራር ፡ከአገር ቤት ነዋሪው እና
ከከተማና ከአገር ውጭ ከሚኖሩ የእዣ ተወላጆች እና ወዳጆች ጋር በመመካከር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚቀየስ ይሆናል።
የተቀየሱት ከችግር መውጫ መንገዶች የጋበርና የተወላጁ የቤት ስራ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል።
ጋበር ቅዳሜ ህዳር 01 ቀን 2016ዓም በሁሉም የእዣ ወረዳ ቀበሌዎች ይጠበቃል።
ብዙ ኣይነት ጉዞ ወደ ትውልድ ቀዬ ተደርጎ ያውቅ ይሆናል።ለመስቀል ለአረፋ እንዲሁም ለዓመታዊ ክብረ በዓልና ለለቅሶም ጭምር።
እነዚህ ጉዞዎች ዓላማቸው የተለያየ ስለሆነ ከዚህኛው የጋበር ጉዞ በእጅጉ ይለያሉ።
ለምሳሌ የመስቀልና የአረፋ በዓል ለማክበር የሚደረገው ጉዞ ፉክክር የበዛበት ከእኛ ይልቅ እኔ የሚጎላበት ሲያልፍም ኢኮኖሚያዊ አቅም
ማሳያ(በተለይ የስጋ ከብት ግዢ በሚፈፀምበት ጊዜ) ነው።
የአሁኑ የጋበር ‘ቅዱስ ጉባዔ’ ከእኔ ወደ እኛ እየተቀየረ ያለ ጉዞ ነው። አንጋፋ የልማት ኣባቶች ለወጣቶች ልምድ የሚያካፍሉበት የተማሩና
የተመራመሩት አንጋፋ ምሁራን ለወጣቶች የአገር ፍቅርና ለወጡበት ማህበረሰብ ማገልገልን/አለማገልገልን እንደሚያስቆጭ/ እንዲሁም
ከምንም በመነሳት በጥረትና በትጋት ከሀብት ማማ ላይ ከሚገኙት ባለሀብቶቻችን በመስጠት የሚገኘው ደስታና ዝቅ ብሎ ገንዘብንም
ጊዜም ጉልበትም መስጠት የሚሰጠው ስሜት ለታዳጊ እና ወጣቶች ተግባራዊ የበጎነት ስልጠና የሚሰጥበት ጉባኤ ነው። ወላጆች ደግሞ
ይህን ጅምር በማየታቸው ሀሴት በማድረግ የጎደለው ክፍተት እንዲሟላ ተንከባክበውና አስተምረው ያሳደጉትን ልጃቸው ባለሀብትና
ምሁር ልጃቸው ‘’ምር ይፈዝ ምር ይብስ’’ ለማለት ነውና ህዳር አንድ ለጋበር ጠንሳሾች አደራጆች ደጋፊዎች እና አባላት የስኬት መሰረት
የሚጣልበት የጋበር ራዕይ ላም አለኝ በሰማይ ሳይሆን የሚታይና የሚጨበጥ እንደሆነ ማሳያ ታሪካዊ ቀን ነው።የትውልድ አካባቢን
እንደዚህ ለማገልገል መብቃት መታደል ነው።
ጋበር እንደ 5G
ጋበር የጉራጌን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ የሙከራ ስርጭቱን ከእዣ ጀምሯል።
ጋበር በትምህርት በጤና እና በግብርናው ዘርፍ ዕምርታዊ ለውጥ በማምጣት ጉራጌን ከርሀብና ከኋላቀርነት ነፃ ለመውጣት ትክክለኛው መንገድ ነው።






©2023. የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከአገና ኮንስትራክሽን እና ኢደስትሪያል ኮሌጅ ጋር በመተባበር. All Rights Reserved.