የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

==========================

ከ12ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንዳሉ የሚነገርላቸው ጥንታዊ ፡ ታሪካዊና ለቱሪስት ቀልብ የሚስቡ ቅርሶች ባለቤት የሆነችው እዣ ወረዳ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለፀ ።

የበርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶች መገኛ የሆነችው እዣ ወረዳ የትሪስት መዳረሻ እንድትሆን ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት የወረዳው ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት ገለፀ ።

የፅ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ የሺ ተካ እንዳሉት እዣ ወረዳ የበርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህቦች መገኛ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ምቹ እና አዋጪ ወረዳ መሆኗ በዘርፉ ውጤታማ የሆኑ ኢንቨስትመንቶች ህያው ምስክሮች ናቸው ።

በወረዳው የሚገኙ መስህቦች በማልማትና በመጠበቅ እና በማስተዋወቅ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑም ይገኛሉ ሲሉ ሀላፊዋ አክለው ገልፀዋል ።

በወረዳው ከሚገኙ የተፈጥሮ መስህቦች መካከል ፡-ትረር ፏፏቴ፣ፎቅራ ፏፏቴ፣እንደናኪያር ፏፏቴ ውብና ማራኪ ጀፎሮዎችና ደኖች ይገኙበታል ያሉት ሀላፊዋ ከሰው ሰራሽ መካከል ደግሞ ፡-አትርፎ ደብረ ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴደሪል ፣ ዲር መስጅድ ፡ ሻም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፡ የገሞ መስጅድ ፣ የደረሬ ደብረ ብስራት ቅ/ገብርኤል “ገዳም ወደብር” ፡ ገጨ ሩፋኤል ገዳምና ቆጠር ገድራ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም እና ሌሎችም መጥቀስ እንደሚቻልም ወ/ሮ የሺ አብራርተዋል ።

በመሆኑም እነዚህን ቀልብ የሚስቡና መንፈስን የሚያድሱ የቱሪስ መዳረሻ መስህቦቻችን መኖራቸው ደግም ለኢንቨስትመንት ምቹ በመሆኑ ባለሀብቱ ወደ እዣ ወረዳ መጥቶ ኢንቨስት በማድረግ የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ሀላፊዋ መልእክት አስተላልፈል።

በእዣ ወረዳ ከሚገኙ የቱሪስት መስህቦች በጥቂቱ በወፍ በረር ለማስተዋወቅ ያክል :-

1 የአትርፎ ደብረ ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን፦ በእዣ ወረዳ ገደብ ቀበሌ ልዩ ስሙ የገረሙጀ ሲሆን; ከዞናችን ዋና ከተማ ከወልቂጤ በ52 ኪ ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ7 ኪ ሜ ርቀት በስተ ምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል፡፡
2 የገጨ ደብረ መድሀኒት ቅዱስ ሩፋኤል አንድነት ገዳም፦ በእዣ ወረዳ በዴሰነ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገጨ ጎጥ ሲሆን; ከዞናችን ዋና ከተማ ወልቂጤ በ39 ኪ ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ3 ኪ ሜ በስተምዕራብ አቅጣጫ ያገኙታል፡፡
3 የገሞ መስጅድ፦ በእዣ ወረዳ በጉየና የስዋ ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ53 ኪ ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ11 ኪ ሜ በስተምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል።
4 የደረሬ ደብረ ብስራት ቅ/ገብርኤል “ገዳም ወደብር” ከወረዳው ዋና ከተማ አገና በስተምስራቅ አቅጣጫ በ8ኪሜትር ገደማ ይገኛል።
5 የቆጠር ገድራ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም፦ በእዣ ወረዳ በቆጠር ገድራ ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ54 ኪ ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ12 ኪ ሜ በስተ ምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል።
6 የዲር መስጅድ፦ በእዣ ወረዳ በቦዠባር ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ62 ኪ ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ20 ኪ ሜ በስተምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል። 6 የቆጠር ገድራ ደን፦ በእዣ ወረዳ በቆጠር ገድራ ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ54 ኪ ሜ እና ከአገና ከተማ በ12 ኪ ሜ በስተምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል።
8 አምባ ደን፦ በእዣ ወረዳ በዌራ ደባነ ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ44 ኪ ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ2 ኪ ሜ በስተምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል።
8 ትረር ፏፏቴ፦ በእዣ ወረዳ በዴሰነ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፊየት ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ44 ኪ ሜ እና ከወረዳችን ዋና ከተማ አገና በ2 ኪ ሜ በስተምዕራብ አቅጣጫ ያገኙታል።
10 ኩየ ትክል ድንጋይ፦ በእዣ ወረዳ በዌራ ደባነ ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ50 ኪ ሜ እና ከአገና ከተማ በ8 ኪ ሜ ርቀት በስተምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል።
11 እንደናኪያር ፏፏቴ፦ በእዣ ወረዳ በዌራ ደባነ ቀበሌ ሲሆን; ከወልቂጤ በ49 ኪ ሜ እና ከአገና ከተማ በ7 ኪ ሜ ርቀት በስተምስራቅ አቅጣጫ ያገኙታል።
ከነዚህም በተጨማሪ እጅግ በጥበብ ተሰርተው በቀድሞ አባቶችን የተቀየሱ ጀፈረዎች ፡ ብዙ ቅርስ የያዙ ዋሻዎችና ሌሎችም መገኛ ናትና ኑ እዣ ወረዳ ጎብኙ ፡ እንቨስትም አድርጉ ውጤታማ ይሆናሉ ። መረጃው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ለበለጠ መረጃ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮቻችን የምናደርሳቸው መረጃዎች ይከታተሉን !!