የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

====================================

በ12ኛ ከፍል ፈተና ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ማስተካከል ይችላሉ‼️

በ2015የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳወ ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሰታወቀ።

በልዩ ሁኔታ በአዳማና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር ለሚፈል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ በመሆኑ ምርጫቸው ውስጥ በማካተት መመደብ እንደሚችሉም ገልጿል።

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት ለመማር ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርትቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚቻልም አሳስቧል።