የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ9 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ9 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ9 ሚሊዮን 36 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ በ2018 ዓ.ም ለሚያከናውነው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።

መራጮች በምርጫ ጣቢያዎች በአካል በመቅረብ እንዲሁም “ምርጫዬ” በተሰኘው ዘመናዊ መተግበሪያ አማካኝነት ምዝገባቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቋቋሙት 52 ሺህ 773 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ46 ሺህ 757ቱ ላይ የመራጮች መመዝገቢያ ቁሳቁሶች በወቅቱ ደርሰው ምዝገባው በስኬት እየተካሄደ ነው።

በቀሪዎቹ የምርጫ ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶች ምዝገባው የዘገየ ቢሆንም፤ ቁሳቁሶቹ በደረሱባቸው አካባቢዎች ሁሉ ሂደቱ መጀመሩን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።