
=========================================
የጨረራ ምንነት
ጨረራ(Radiation)
በሞገድ (wave) መልክ ወይም በአነስተኛ ልዩ ልዩ ቅንጣቶች(Particles) ኤነርጂ ከቦታ ወደ ቦታ የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡
የጨረረ ዓይነቶች
አዮን ፈጣሪ ጨረራ እና አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ ጨረራ ተብለው በ2 ይከፈላሉ
1.አዮን ፈጣሪ ጨረራ ማለት ጨረራ በቁስ (matter) ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ አዮን መፍጠር የሚችሉ ሲሆኑ
የጋማ፣የቤታ፣ የአልፋ፣ የኒውትሮን የኤክስሬይ አዮን ፈጣሪ የሆኑ የጨረራ ዓይነቶች ናቸው
2.አዮን ፈጣሪ ያልሆነ ጨረራ ማለት ጨረራ በቁስ (matter) ውስጥ ሲያልፉ አዮን የማይፈጥሩ ሲሆኑ የተለያዩ የራዲዮ ሞገዶች፣ ልዕለ ሃምራዊ፣ ታህተቀይ፣ ብርሃን ሌዘር አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ ዓይነቶች ናቸው፡፡
የጨረራ መንስዔዎች
በቁስ ውስጥ ጨረራ በሁለት ቦታ በአቶሚክ ሼል እና በኒዩክሌስ ውስጥ ሊፈጠር ይችላል አተሞች ለመረጋጋት በሚያደርጉት በኒየክሌስ ውስጥ ጨረራ የሚፈጠረው በአተሞች አለመረጋጋት ሲሆን ይህም በአቶም ውስጥ ያለው የፕሩቶን ቁጥር ከኒዩትሮን ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በጣም ከፍ ወይም በጣም ዝቅ ሲል ነው እንቅስቀሴ በቅንጣጢት(Particles)መልክ እንደ አልፋ፣ቤታ፣ኒዩትሮን ጨረራ ሞገድ(Electromagnetic Wave) እንደ ጋማ ጨረራ ይለቀቃሉ ኤክስሬይ ደግሞ በአቶሚክ ሼል ውስጥ ኤሌክትሮኖች ከአንዱ ሼል ወደ
ሼል በሚያደርጉት ሽግሽግ በሚፈጠር ኤነርጂ ልዩነት ምክንያት ይፈጠራል፡፡
- የጨረራ ምንጮች
1.በተፈጥሮ የሚገኙ የጨረራ ምንጮች
2.ሰው ሰራሽ የጨረራ ምንጮች
ተፈጥሮ የጨረራ ምንጮች የሚባሉት ፀሀይ፣ ከዋክብት፣ በምድር ላይ የሚገኙ ጨረራ አመንጪ ማእድናት ናቸው
የተፈጥሮ የጨረራ ምንጮች
ዩኒቨርስ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ያሉ ናቸው
መጠናቸው ከቦታ ቦታ ከሀገር ሀገር ይለያያሉየ
ጨረራ ጥቅም
በሃይል ምንጩ ዘርፍ
- በኃይል ምንጭነት፣
- ለኤሌክትሪክ አቅርቦት
- የባሕር ውኃን ከጨው ለመለየት
- ለጠፈር ጉዞና ምርምር
- በባሕር ላይ ለሚደረግ የመርከብ ጉዞ
የምርምር ማብለያ (Research Reactors )
¨ በትምህርት ተቋማት ስልጠና ለመስጠት
¨ ለምርምር
¨ በሕክምናና በኢንዱስተሪ ውስጥ የሚያስፈልጉ
¨ ራዲዮ አይሶቶፖችን ለማቀነባበር
¨ የመሳሪያዎችን ጥራት ለመለካት
በግንባታው ዘርፍ
- የመንገዶችን
- የሕንፃ መሰረቶች፣
- የድልድዮች
- ጥራትና ደረጃ ለማረጋገጥ ለውኃ እና ማዕድን ፍለጋና ልማት፣
መንገድ ስራ ላይ በአይሶቶፕ ሀይድሮሎጂ የውኃውን ዕድሜ፣መነሻ ቦታና የውኃውን የፍሰት እንቅስቃሴ ለማወቅ አይሶቶፖች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
- · በኢንዱስትሪ የምርት ጥራትንና የሥራ ሂደቶችን ለመቆጣ(Quality tests, Non-Destructive Tests) -NDT-
ነዳጅ ፍለጋ
በኢንዱስተሪያል ራዲዮግረፊ ተግባር የኤክስ ሬይና ጋማ ሬይ ጥራትን ለመቆጣጠር ጥቅም ይሰጣሉ
- የራዲዮግራፊክ ፍተሻ
- የቅሪት አካላትን ዕድሜ ለማወቅ
- የሻንጣና የጭነት መፈተሻ
ጨረራ በሕክምናው ዘርፍ ያለው ጥቅም
የራጅ ምርመራ
- የኒዩክሌር ሕክምና
- የጨረራ ሕክምና
ኒዩክሌር መድኃኒቶች
ጨረራ ጉዳቶች
አዮን ፈጣሪ ለኾኑ የጨረራ ዓይነቶች አለአግባብ መጋለጥ በሰው ጤና ላይ በአጭር ጊዜ የአካል ጉዳትና ሞት፣
ወደ ትውልድ የሚተላለፉ ልዩ ልዩ የጤና ችግሮች
በረጅም ጊዜ ሊከሰት የሚችል ካንሰር ሊያመጣ ይችላል፡፡
አዮን ፈጣሪ ላልሆኑ የጨረራ ዓይነቶች አለአግባብ መጋለጥ
በሰው ጤና ጣይ ምርምሮች የሚካኼዱበት ሆኖ የሕዋሶቻችን ሙቀት እንዲጨምር
ለሚያደርግ በረጅም ጊዜ ሊያስከትለው የሚችል ጉዳት ይኖረዋል
የጨረራ ሥነ– ሕይወታዊ ተፅዕኖጨረራው ዓይነት
- የጨረራው ኃይልና የውስድ መጠን አወሳሰድ
የተጋለጠው አካል(ለጨረራ ያለው ስሜታዊነት)
የጨረራ ውስድ መጠን የሚያስከትለው ሥነ–ሕይወታዊ ተፅዕኖ የሚወስኑ ምክንያቶች
ጨረራ መከላከልና ደኅንነት መርሆዎች
ICRP እርስ በርሳቸው የሚዛመዱ 3 መሰረታዊ
የጨረራ መከላከልና ደህንነት መርሆዎች(Principles) ተግባራዊ እንዲደረጉ ይጠቁማል፡፡
እነሱም፣
ጥቅሙና ጉዳቱ ማመዛዘን(Justification)
የጨረራ መጠን በመቀነስ አጥጋቢ ውጤት ማግኘት (Optimization) –ALARA Principle
እናከ ተፈቀደ የጨረራ ውስድ መጠን አለማለፍ(Dose Limitation) የሚባሉ ናቸው፡፡
ለጨረራ የምንጋለጥባቸው መንገዶች
ለጨረራ የምንጋለጥባቸው መንገዶች 2 ናቸው፡
ውስጣዊ መጋለጥ በትንፋሽ በምግብና ፈሳሽ በቆሰሉ ወይም በተቆረጡ የቆዳ አካሎች
ውጫዊ መጋለጥ በጋማ በራጅ በኒዩትሮንና በሌሎችም
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ ክትትልና አቅም ግምባታ ዳይሬክቶሬት
ስልክ ፡-0113290735
Email ፡-Edjaworedasitoffice@gmail.com
website፡- Ezhaguraghe.gov.et
Telegram :-የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤጽ( Ezhaworda SIT office )






