
======በተቋማት ውስጥ የወረቀት ስራን አስቀራለሁ – በላይ አላምነህ
ሰፊ ቤተሰብ ውስጥ ያደኩኝ ነኝ፡፡
የተወለድኩት ጎጃም ዳሞት ነው፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምኀርቴን 60 ኪ.ሜ ተጉዤ ነው የተማርኩት፡፡
የ3ተኛ እና የ4ተኛ ክፍል ፤ የ5ተኛ እና የ6ተኛ ክፍል ትምኀርትን ‘ደብል‘ መትቼ ነው ያለፍኩት፡፡
በሁለት ዓመት ውስጥ የአራቱን ክፍል ተምሬአለሁ፡፡
ሁሌም አንደኛ የምወጣ ተማሪ ነኝ፡፡
ዲግሪ ለመያዝ 12 አመት ነው የፈጀብኝ!
የሁለተኛ ደረጃ ትምኀርት ቤት ሥማር ከቤተሰብ ርቄ ነው የኖርኩት፡፡
በእግሬ የአራት ሰዓት መንገድ ተጉዤ ÷ እንጀራ ጋግሬ ነው የምማር የነበረው፡፡
በትምኀርት ድክመት የነበረኝ የኮምፒውተር እውቀቴ ላይ ነበር፡፡
አዳማ ዩኒቨርስቲ ስገባ የሶፍትዌር ምህንድስና ለመማር ወሰንኩ፡፡
የልጅነት የኤሌክትሪክ ኢንጅነር የመሆን ፍላጎቴን ተውኩት፡፡
ከአዳማ ዩኒቨርስቲ በሶፍትዌር ምህንድስና ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች አንዱ ነበርኩ፡፡
የመጀመሪያ ዲግሪዬን ለመያዝ ከሚጠይቀው 16 አመት እኔመጨረስ የቻልኩት በ 12 አመት ነው፡፡
ከአንዴም ሁለት ጊዜ ደብል በመምታቴ የሚፈጀውን ጊዜ መቀነስ ችያለሁ፡፡
በውጪ አገራት ሄዶ ለመማር እድሉ ነበረኝ እኔ ግን መማርም ማስተማርም የምፈልገው በኢትዮጵያ ነው!
በአዳማ እና በባሕርዳር ዩኒቨርስቲ በሶፍትዌር ምሕንድስና የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዬን ከተማርኩ በኃላ ውስጤ ጥሩ ተሰማው፡፡
በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በመምኀርነት ማገልገል ከጀመርኩ አምስት አመት ሆኖኛል፡፡
ቢሮክራሲ ደሕና ሰንብት!
ዲጂታል ሌተሪንግ የመወዳደሪያ ፕሮጀክቴ የደብዳቤ ÷ የቲተር ÷ የፊርማ እና ኃላቀር አሰራሮችን በዲጂታል የሚተካ ዘመናዊ የተቋማት አገልግሎት ማስተካከያ መላ ነው ይዤ የመጣሁት፡፡
ቢሮክራሲን አሽቀንጥሮ ጥሎ ÷ መስተጓጎልን በፍጥነት የሚተካው የዲጂታል ሌተሪንግ አሠራርን ከተማሪዎቼ ጋር ሁኜ በኢትዮጵያ ተቋማት ውስጥ መትከል ዕለት ዕለት የምሰራበት ጉዳይ ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክቴ የአገራችንን ተቋማት ከኃላቀርነት የሚታደግ ስለሆነ ፕሮጀክቴ አሸናፊ እንደሚሆን እተማመናለሁ፡፡
ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር የፍፃሜ ኘሮግራም እሑድ ጥር 3 ይካሄዳል። ኘሮግራሙ በኢቢሲ በቀጥታ ይተላለፋል።







