






በእዣ ወረዳ አገና ከተማ የ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የኢድ ሶላት ሥነ-ሥርዓት በሰላም ተጠናቀቀ።
መጋቢት 11/2018 ዓ.ም
የእዣ ወረዳ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለአንድ ወር ያህል ሲፆሙት የቆዩትን የረመዳን ወር በማጠናቀቅ፣ 1447ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል በአገና ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
የእዣ ወረዳ መጅሊስ ሰብሳቢ ሼህ ሀሰን ሸሪፍ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት መገለጫ መሆኑንና በረመዳን ወር የታየው የመረዳዳትና የመተጋገዝ ባህል በበዓሉም ወቅት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና አቅም የሌላቸውን ወገኖች በማሰብ እንዲከበር አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለት በእዣ ወረዳ አገና ከተማ ወጣቶች ማዕከል በማለዳው የተጀመረው የኢድ ሶላት ሥነ-ሥርዓት ላይ የእምነቱ አባቶች የእዣ ወረዳና አገና ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተገኝተዋል።






