የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን #እዣ ወረዳ #ዋሳማር ቀበሌ

በጉራጌ ዞን #እዣ ወረዳ #ዋሳማር ቀበሌ አዘር መንደር የጉራጌ ባህላዊ ጎጆ ቤቶችን ከዘመናዊ መኖሪያ ቤት ግንባታ ጋር በመቀናጀታቸው ለአካባቢው ልዩ ውበት አጎናፅፎታል ።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ ጨምሮ የእዣ ወረዳ አመራሮች በባለሀብቶቹ የተገነቡ ግንባታዎች ጎብኝተዋል ።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ በጉብኝቱ ወቅትም እንዳሉት የጉራጌ ብሄረሰብ እጅግ የሚደነቅ የበርካታ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ነዉ፡፡ ከዚህ ዉስጥ ባህላዊ የሳር ቤት(ጎጆ ቤት) አሰራር አንዱ ነዉ፡፡

ይህንን ግንባታ በባለሀብቱ ደረጃ መገንባቱ የሚበረታታ ሲሆን ግንባታው ከገጠር ኮሪደር ልማት ጋር ያሳለጠ እንደሆነም ሀላፊዋ አመላክተዋል።

በጉራጌ ብሄረሰብ የጎጆ ቤት ሥራ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወን ተግባር ሲሆን አባቶች ዘመናዊ የምህንድስና ትምህርት ምን እንደሆነ ሳያዉቁ የሳር ቤት አወቃቀርና የመንደር አመሰራረት እንዲሁም የቤት አያያዝና አጋጌጥ እጅግ የሚገርም እንደሆነም ሀላፊዋ ተናግረዋል።

የጉራጌ ባህላዊ ቤቶች በአራት ደረጃ የሚከፈሉ ሲሆን እነሱም ጎየ(ትልቅ ቤት)፣ ኸራር(እልፍኝ ቤት)፣ ዘገር(የሙሹሮች ቤት) እና አራተኛው ደረጃ ቀለል ባለ መልኩ የሚሰራ እና ለከብቶች ገለባ ማስቀመጫነት የሚያገለግል “ሰንቃላ” በመባል የሚታወቀው ነው።

ይህ የምንመለከተው አካባቢ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ዋሳማር ቀበሌ አዘር መንደር ላይ የጉራጌ ባህላዊ ጎጆ ቤቶች ከዘመናዊው መኖሪያ ቤት ግንባታ ጋር ተቀናጅተው ለአካባቢው ልዩ ውበት ፈጥረዋል ያሉት ወ/ሮ መሰረት እንደዚህ አይነቱ የባህላቸው ተቆርቋሪዎችና የትውልድ አካባቢያቸውን ማይረሱት ጀግኖች ማበረታታት ይገባልም ብለዋል።