





በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ዳርቻና ዝግባቦቶ ከተማ መዘጋጃ ቤት በገጠር ኮሪደር ልማት ሞዴል የአርሶ አደሮች መንደር ግንባታ ቦታ ርክብክብ ተካሄደ ።
ሰኔ 14/2018 ዓም
የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም አወል በርክብክብ ስነስርዓቱ ወቅት እንዳሉት ሞዴል የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ግንባታ ቦታ ርክብክብ በተካሄደበት ወቅት እንዳሉት መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ።
የሚከናወኑ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎች አስፈላጊው የመሰረተ ልማት እንዲሟላ ከማድረግ ባለፈ አርሶ አደሩ ዘመናዊና የተመቸ ኑሮ እንዲመራ ያስችላል ያሉት አቶ ኢይራሂም ሞዴል የአርሶ አደሮች መንደር ግንባታ አካባቢያዊ ሀብቶችን በመጠቀም እንደሚከናወንና የተከቡትንም አካል ለፕሮጀክቱ መሳካት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የእዣ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው አየለ በበኩላቸው ለዚህም ግንባታ የወረዳው መንግስት በዳርቻና ዝግባቦቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በነፃ ቦታ ያመቻቸ ሲሆን በዚህም እያንዳንዱ አርሶ አደር 500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ማእድ ቤት ፡ የእንሰሳት መጠለያ፣ ንፁህ ሽንት ቤትና ሻወር ይኖረዋል ብለዋል ።
አቶ ጌታቸው አያይዘውም በሚገነባው መኖሪያ ቤትም በግቢው ውስጥ የጓሮ አትክልትና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተካተውበት ዘመናዊ የእርሻና የኑሮ ስታንዳርድ ይፈጠራልብለዋል።
ቦታው የተረከቡ አካላትም በስታንዳርዱ መሰረት በአጭር ጊዜ እንደሚገነቡም ተስማምተዋል።






